Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር

Now Open
  • Viewed - 81

ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር

Now Open
  • Viewed - 81

Description

ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅት/ቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት  ይፈልጋል።

1. የጨረታ ዝርዝር

 

መግለጫ መስፈርት/ብዛት
የሚፈለገው ብዛት 4 ሚሊየን ኪሎ (4000 ቶን) ነጭ የተጣራ ስኳር
የጥራት ደረጃ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ፣ ለምግብና መጠጥ ምርት ተስማሚ፣ ከብክለት የጸዳ፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫዎችን የተከተለ።
ማሸጊያ እርጥበትን መቋቋም በሚችል ማሸጊያ መታሸጉን ማረጋገጥ።
የጥራት ማረጋገጫ ሰነድ ለእያንዳንዱ ባች የትንታኔ ሰርተፍኬት (Certificate of Analysis) ማቅረብ።
የመተካት ግዴታ ጉድለት ያለባቸውን አቅርቦቶች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ መተካት ይኖርባቸዋል።
አሰጣጥ በቅድመ-ስምምነት መሠረት ስኳሩን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

 

2. የግዴታ መስፈርቶች (Required Documents)

 

ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

  • በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት
  • የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት

 

3. የጨረታው ጊዜና አድራሻ

 

እርምጃ ዝርዝር ቀን/ሰዓት
የጨረታ ሰነድ መውሰድ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል እስከ ጥቅምት 28 ቀን፣ ሰባት ሰዓት (1፡00 ከሰዓት) ድረስ።
የጨረታ ማቅረቢያ (Submission) በአካል ወደ ዋና መስሪያ ቤት ወይም በኢሜል አድራሻ እስከ ጥቅምት 28 ቀን፣ ስምንት ሰዓት (2፡00 ከሰዓት) ድረስ።
የኢሜይል አድራሻ factoryprocurement@habeshabreweries.com
አድራሻ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር፣ ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት፣ አዲስ አበባ።
ስልክ ቁጥር 0965683654 / 0911478704

ማሳሰቢያ: ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የጨረታውን የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት በጥቅምት 28፣ ከሰዓት 2፡00 ሰዓት መሆኑን በማረጋገጥ ሰነድዎን ያስገቡ።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.