Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In
Now Open
  • Viewed - 80
Now Open
  • Viewed - 80

Description

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ /አሁን በሚገኙበት ይዞታ/ ላይ እንዳሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ይህ ከአቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ የመጀመሪያ ጊዜ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ነው።


 

🚗 አቢሲንያ ባንክ አ.ማ፡ የተሽከርካሪዎች ሐራጅ ሽያጭ

 

 

📌 ለሐራጅ የቀረቡ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/መያዣ ሰጪ ስም የሰሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪው ዓይነትና ዘመን ሞዴል የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)
1. አቶ በርሄ ገ/መድህን ኢት-03-94574 ቻይና፣ ሲኖ ሆዎ 371 የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ቦቴ (እ.ኤ.አ 2016 GC) ZZ1257S4341W 6,562,500.00
2. አቶ በርሄ ገ/መድህን ኢት-03-29252 ኢትዮጵያ፣ የHH ኢንጂነሪንግ ስሪት የሆነ የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ተሳቢ (እ.ኤ.አ 2017 GC) HHENG 3,534,300.00

ማሳሰቢያ: ተሽከርካሪዎቹ ተለያይተው አይሸጡም

 

📅 የጨረታው ቀንና ሰዓት

 

  • የሐራጁ ቀን: ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
  • የምዝገባ ሰዓት: ከጠዋቱ 4፡30 – 5፡30
  • የጨረታ ሰዓት: ከጠዋቱ 5፡30 – 6፡00

 

📜 የጨረታው መመሪያዎች

 

  1. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
    • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
    • የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለየብቻ መሰራት አለበት (ንብረቶቹ ተለያይተው ባይሸጡም)።
  2. ክፍያ:
    • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
    • ሳይከፍል ከቀረ፣ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  3. ተጓዳኝ ክፍያዎች (በአሸናፊ የሚሸፈኑ):
    • አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
  4. ብድር የመስጠት ዕድል:
    • ባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አሸናፊ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  5. ንብረት መጎብኘት:
    • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።

 

📍 የጨረታው ቦታ

 

  • አድራሻ: አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።

 

📞 ለተጨማሪ መረጃ

 

  • ስልክ ቁጥር: 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.