🧾 የሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አ.ማ፡ የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
የአክሲዮን ማኅበሩ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሂሳብ መዝገብን በIFRS (International Financial Reporting Standards) መሠረት ኦዲት የሚያደርጉ ሰርተፋይድ ኦዲት ድርጅቶች አወዳድሮ የአገልግሎት ስምምነት ለመፈፀም ይፈልጋል።
✅ ተጫራቾች (የኦዲት ድርጅቶች) ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
- የሙያ ፈቃድ: በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለዉ የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን።
- ንግድ ፈቃድ: ወቅታዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ ያለዉ።
- የሙያ ማረጋገጫ: የታደሠ የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ ያለዉ።
- ልምድ: የሥራ ልምድ መግለጫ ማቅረብ።
- ብቃት ያለው ባለሙያ: የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል።
📅 የጨረታው ጊዜና ቦታ
- ሰነድ ማቅረቢያ (መዝጊያ) የመጨረሻ ቀን: ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት።
- የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት: ጨረታዉ በተጠናቀቀዉ ቀን በ11ኛ ቀን በማግሥቱ 4፡00 ሰዓት ላይ።
- ሰነድ ማቅረቢያ ቦታ: ሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር (ልዩ ስሙ ሸገር ግራንድ ሞል)
📜 የማመልከቻ ሂደት
- የመወዳደሪያ ሰነዶችን በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ዉስጥ ማቅረብ።
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል።
📞 አድራሻ እና ስልክ ቁጥር
- አድራሻ፡ ሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር፣ ሸገር ግራንድ ሞል
- ስልክ፡ 0911 41 11 19 / 0910 61 52 26