Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

በሎት አንድ ለሁለተኛ ግዜ እና በሎት ሁለት ለሶስተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ

Now Open
  • Viewed - 14

በሎት አንድ ለሁለተኛ ግዜ እና በሎት ሁለት ለሶስተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ

Now Open
  • Viewed - 14

Description

ዳሽን ባንክ አ.ማ.  በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሎት አንድ ለሁለተኛ ግዜ እና በሎት ሁለት ለሶስተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/039/2018

 

  1. ተጫራቾች ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
  5. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  6. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሽን ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ10ኛው ቀን ማለትም ጥር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
  9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ በ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  10. ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-465 5552 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ዳሽን ባንክ አ.ማ.

አዲስ አበባ

ሎት አንድ (የሁለተኛ ዙር ጨረታ)

ተ.ቁ የንብረቱ ዓይነት መለኪያ ጠቅላላ ብዛት
1 Kama small generator በቁጥር 05
2 Kama big generator በቁጥር 01
3 Single pedestal Table በጥቅል በጥቅል
4 Managerial Table በጥቅል በጥቅል
5 Guest Chair በጥቅል በጥቅል
6 Lowback chair በጥቅል በጥቅል
7 Safe Box በቁጥር 02
8 Fire resistant four drawer በቁጥር 05
9 Fire extinguisher በቁጥር 07
10 Storage cabinet በጥቅል በጥቅል
11 Note counting for tellers በቁጥር 142
12 Note counting for cashers በቁጥር 17
13 Passbook Printer በቁጥር 27
14 Multi-currency detector በቁጥር 32
15 Foreign currency display በቁጥር 13
16 Scanner machine በቁጥር 19
17 Switch በቁጥር 12
18 Monitor በቁጥር 40
19 Kyocera Photocopy በቁጥር 26
20 Kyocera Printer በቁጥር 20

 

 

 

ሎት ሁለት (የሶስተኛ ዙር ጨረታ)

ተ.ቁ የንብረቱ ዓይነት መለኪያ ጠቅላላ ብዛት
1 UPS በቁጥር 07
2 Adding Machine በቁጥር 07
3 STORAGE CABINET በቁጥር 08
4 NOTE COUNTING MACHINE FOR TELLER በቁጥር 261
5 Child bed በቁጥር 14
6 Kama small generator በቁጥር 05
7 Kama Big generator በቁጥር 02
8 PASSBOOK PRINTER በቁጥር 39
9 Kyocera printer በቁጥር 36
10 HP LASERJET PRINTER በቁጥር 05
11 SCANNER MN በቁጥር 15
12 MONITOR በቁጥር 31

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.