Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች (TLS) ግንባታ ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 11

የጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች (TLS) ግንባታ ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 11

Description

የጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች (TLS) ግንባታ ግልጽ ጨረታ

ኢማጂን ዋን ዴይ (Imagine 1 Day – I1D)

የጨረታ መለያ ቁጥር፦ Tig/i1d/Finland/UNICEF/002/2026

ኢማጂን ዋን ዴይ (I1D) በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች (Temporary Learning Spaces – TLS) ግንባታ ብቃት ያላቸውን ተቋራጮች በሦስት ምድቦች (Lots) አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1. የግንባታ ቦታዎች ዝርዝር (Lots)

ምድብ (Lot) ወረዳ የትምህርት ቤቶች ስም
Lot 1 ራያ ጨርጨር ቀርሶሌ፣ ጻዕዳ ማይዳ፣ ዶዶታ፣ ቁሌታ እና ማሩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።
Lot 2 ኮረም ቆላ ጽሕዲ እና መስቆተ ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።
Lot 3 ዛታ ዳራ ማርያም፣ በቀዳ፣ ዲንቃ እና ዳራ ወላኩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።

2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  • ደረጃ (Grade)፦ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሕንፃ ወይም ጠቅላላ ተቋራጭ (BC/GC Grade 5 & Above)።

  • ልምድ፦ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ 5 ተመሳሳይ የክፍል ግንባታ ፕሮጀክቶችን መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) በኩል ያከናወነ።

  • ሕጋዊ ሰነዶች፦ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የቲን (TIN) ሰርተፍኬት፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የቫት (VAT) ዲክላሬሽን።

  • የሥራ ጊዜ፦ ውል በተፈረመ በ 7 ቀናት ውስጥ ሥራ መጀመርና በ 45 የካላንደር ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ ይኖርበታል።


3. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

  • መጠን፦ ከጠቅላላ ዋጋው (ቫትን ሳይጨምር) 5%

  • ዓይነት፦ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (ጥሬ ገንዘብና የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የላቸውም)።


4. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና መዝጊያ ቀን

  • የሰነድ ዋጋ፦ የማይመለስ ብር 600.00

  • ሰነድ መገኛ፦ በመቀሌ በሚገኘው የኢማጂን ዋን ዴይ የትግራይ ክልል ማስተባበሪያ ቢሮ ከመጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (March 30, 2026) ጀምሮ።

  • የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (April 08, 2026) ከጠዋቱ 3:00 (9:00 AM) ሰዓት።

  • የመክፈቻ ጊዜ፦ በዕለቱ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 (9:30 AM) ሰዓት።


5. አድራሻ እና መገናኛ

  • ቦታ፦ መቀሌ፣ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ (ዓዲ ሓውሲ ገበያ)፣ ሕዳሴ ቀበሌ፣ ከሊባኖስ ሆቴል 250 ሜትር ወደ ደቡብ።

  • ስልክ ቁጥር፦ 034-4-40-37-15 / 034-4-40-49-33

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.