Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ

Now Open
  • Viewed - 319

በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ

Now Open
  • Viewed - 319

Description

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ)

1. የግዥው ማጠቃለያ

 

ዝርዝር መረጃ
ጨረታ አውጪ ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር
የግዥው ዓይነት የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ) አቅርቦት
የዕቃ ርክክብ ቦታ ገርጂ የሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት
የድርጅቱ መብት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

2. የጊዜ ገደብ እና ማስረከቢያ ቦታ

 

እርምጃ ቀን ሰዓት ቦታ
የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ (የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን)
የጨረታ መክፈቻ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም (በዚሁ ዕለት) 4፡30 ጠዋት የድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ

 

3. የገንዘብና የሰነድ መስፈርቶች

 

 

ሀ. የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ)

 

  • መጠን: ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • ቅፅ: በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።

 

ለ. የጨረታ ሰነድ ግዥ

 

  • ዋጋ: ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር)
  • መገኛ: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል
  • የመግዛት ሰዓት: ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሠዓት 7፡00-11፡00) እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን (ጠዋት 2፡00-6፡00)።

 

ሐ. የግዴታ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች እና አቀራረብ

 

ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፡-

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  2. በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ሰርተፍኬት
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ
  • የቴክኒካል ፕሮፖዛል: የዕቃው ዝርዝር መግለጫ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ መቅረብ አለበት።
  • የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል: ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ መቅረብ አለበት።
  • ማሳሰቢያ: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል

 

4. አድራሻ እና ስልክ ቁጥር

 

  • ዋና አድራሻ: ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ፣ ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ፣ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • ከተማ: አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
  • ስልክ ቁጥር: 011-1-569992

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.