Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 374

ግልጽ ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 374

Description

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሐራጅ ማስታወቂያ፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ተሽከርካሪዎች)

 

ይህ ከየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁ.97/1990 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት፣ በመያዣነት የተያዙ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ ነው።


 

1. በሐራጅ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር

 

ተ. ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ የንብረቱ አይነት ሰሌዳ ቁጥር የተመረተበት ዓመት የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት
1 ኦኬ ቦትሊንግ ኤንድ ቢቨሬጅስ አማድል ገበያ የጭነት ተሽከርካሪ ኢት-03-95693 2017 5,049,000.00 02/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡00-4፡00
2 ኦኬ ቦትሊንግ ኤንድ ቢቨሬጅስ አማድል ገበያ ተሳቢ (Trailer) ኢት-03-29595 2017 2,138,400.00 02/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00-5፡00
3 ኦኬ ቦትሊንግ ኤንድ ቢቨሬጅስ አማድል ገበያ የጭነት ተሽከርካሪ ኢት-03-95696 2017 4,870,800.00 02/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 5፡00-6፡00
4 ጉጂ ሃይላንድ ኮፊ ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማኅበር / አቶ ወዴሳ ያቺሲ ቡሉልታ መስቀል ገበያ አውቶሞቢል አአ-02-C43315 2022 3,633,120.00 02/03/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00-9፡00
5 ጉጂ ሃይላንድ ኮፊ ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማኅበር መስቀል ገበያ አውቶሞቢል አአ-03-B58204 2022 4,541,400.00 02/03/2018 ዓ.ም ከሰዓት 9፡00-10፡00

የጨረታ መካሄጃ ቦታ: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203


 

2. የሐራጅ ደንቦች እና ግዴታዎች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (ሲፒኦ):
    • ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (አንድ አራተኛ)ተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል።
    • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው
  2. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታ አሸናፊ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪውን የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
    • ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
  3. ግብር እና ወጪዎች:
    • አሸናፊው በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ይከፍላል
    • አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል
  4. ለንብረት ዝውውር:
    • ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  5. ለንግድ ማህበራት:
    • የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይገባል።
  6. ንብረት መቀበል:
    • ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ አለበት
    • በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት የማይወስድ ሲሆን፣ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ግን ገዢው ኃላፊነቱን ይወስዳል
  7. ንብረት መጎብኘት:
    • ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
  8. የባንኩ መብት:
    • ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.