Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር

Now Open
  • Viewed - 404

በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር

Now Open
  • Viewed - 404

Description

ድርጅታችን የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን በቡና ኤክስፖርት ሥራ ላይ የተሠማራ ሲሆን እ.ኤ.አ ነሐሴ 31, 2025 የተጠናቀቀውንና በ ‘’IFRS’’ የተሠራ የአንድ ዓመት ሂሣብ በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

1. የጨረታው የጊዜ ሰሌዳ እና አጠቃላይ መረጃ

 

ዝርዝር መረጃ
ድርጅት የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን
አገልግሎት የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት)
የጨረታ ማስረከቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት
የጨረታ ማስረከቢያ ሰዓት በሥራ ሰዓት
የአቀራረብ ዘዴ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፕሮፖዛል ማቅረብ
TOR የተዘጋጀውን TOR ከድርጅቱ መውሰድ ይቻላል።

 

2. አስገዳጅ መመዘኛዎች

 

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል:

  1. የሙያ ፈቃድ:ኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ (AABE) ወይም እሱ በሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን።
  2. የንግድ ፈቃድ: በሀገሪቱ ህግ መሠረት ኦዲት ሥራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ: ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።
  4. የምርት ገበያ ምዝገባ:ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን (ECX) የተመዘገበና ማስረጃ ማያያዝ የሚችል።
  5. ተሞክሮ: ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ ምርመራ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት ኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ መሆን።
  6. የባለሙያ ብቃት: የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎች በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ።

 

3. የእውቂያ መረጃ

 

  • አድራሻ: አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 በዩኒየኑ ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ
  • ስልክ: 011 440 7165 እና 0911 40 9994
  • ማሳሰቢያ: ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.