Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 378

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 378

Description

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ቋሚ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጥ ንብረት ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም የንብረቱ አይነትና አገልግሎት የቦታው አጠቃላይ ስፋት (ካ.ሜ) ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)
1 ቡሬ የእንስሳት ምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 3 የተለያየ ስፋት ያላቸው መጋዘኖች 30,000 (ሰላሳ ሺህ) አማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አንጎለላና ጠራ ወረዳ፣ ሰርቲ ቀበሌ 61,854,744.00

 

የጨረታ መካሄጃ ሰዓት እና ቀን

 

  • የጨረታ ቀን: ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም
  • የምዝገባ ሰዓት: 4፡30 – 5፡30
  • የጨረታ ሰዓት: 5፡30 – 6፡00

 

የጨረታ ቦታ

 

  • አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ የፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ።
  • ማሳሰቢያ: መጋዘኖቹ ተነጣጥለው አይሸጡም

 

2. የሐራጅ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (CPO):
    • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ)አቢሲንያ ባንክ ስም በማሰራት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
  2. ክፍያ እና የንብረት አወሳሰድ:
    • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
    • በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
    • በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል
  3. የግብር እና ክፍያዎች:
    • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል
  4. ብድር ማመቻቸት:
    • ባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አሸናፊ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል
  5. መገኘት:
    • ተበዳሪ/መያዣ ሰጪ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል
  6. ንብረት መጎብኘት:
    • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል።
  7. የባንኩ መብት: ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ (ለተጨማሪ መረጃ)

 

  • ስልክ ቁጥር: {011 515 0711} ወይም {011 515 1153}
  • አድራሻ: አዲስ አበባ

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.