Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 329

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 329

Description

ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለ) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር (ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ መኖሪያ ቤቶች)

 

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረቱ አድራሻ (ከተማ/ክ/ከተማ) የቦታው ስፋት (ካ.ሜ) የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጅ የሚከናወንበት ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታው ሰዓት የሐራጁ ደረጃ
1 ወ/ይ አፎሚያ ታደለ ምንይዋብ አ.አ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ቦሌ አራምሳ ሳይት 37.16 2,220,634.51 ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3:30–5:00 ጠዋት 5:00–5:50 በድጋሚ
2 አቶ ወግደረስ መራ እጅጉ አ.አ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ጀሞ 1 ሳይት 30.31 2,365,575.02 ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 7:30–9:00 ከሰዓት 9:00–9:50 በድጋሚ
3 አቶ አቤል ሙሀመድ ይመር አ.አ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ገላን ሳይት 30.31 2,056,606.61 ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3:30–5:00 ጠዋት 5:00–5:50 በድጋሚ
4 አቶ ግርማ ለገሰ ሚጀና ሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዪ ፈጩ ክ/ከተማ 37.16 1,785,404.93 ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 7:30–9:00 ከሰዓት 9:00–9:50 በድጋሚ

 

የሐራጅ መካሄጃ ቦታ

 

  • የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ሰንጋተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ ላይ ነው።

 

2. የሐራጅ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
    • ተጫራቾች የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. ክፍያ እና ቅጣት:
    • አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለበት።
    • ካልከፈሉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ፣ የዋጋውን ልዩነት የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃል
  3. የሐራጅ አዳራሽ ተሳትፎ:
    • ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።
    • የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ መውጣት እና መግባት አይፈቀድም
  4. ግብር እና ወጪዎች:
    • ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም የልማት ገንዘብ ክፍያ እና ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።
    • ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል
  5. ብድር ማመቻቸት:
    • የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል
  6. ንብረት መጎብኘት:
    • ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መጎብኘት ይችላሉ።
  7. የባንኩ መብት: ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ

 

  • ስልክ ቁጥር: ወይም ወይም ወይም
  • አድራሻ: ዘመን ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት (Mexico, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa)

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.