Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት

Now Open
  • Viewed - 79

ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት

Now Open
  • Viewed - 79

Description

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን ለንግድ የሚሆን ቤትን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

1. በጨረታ የቀረቡ ንብረቶች አድራሻዎች

ተ.ቁ የንብረት ዓይነት አድራሻ / የሚገኝበት ቦታ ማስታወሻ
1 መጋዘን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ሁለት መጋዘኖች።  
2 ንግድ ቤት በቸርቸር ጎዳና ትንሣኤ ሕንጻ የሚገኝ።  
3 ቴራዝ (Terrace) ፒያሳ መብራት ኃይል አጠገብ የዘውዲቱ ሕንጻ ላይ የሚገኝ።  
4 ንቃይ ቆርቆሮዎችና የተለያዩ ንብረቶች በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፒያሳ የሚገኘው ኤሌትሪክ ሕንጻ አጠገብ ዘውዲቱ ሕንጻ በሚባለው ግቢ ውስጥ።  
5 ንብረት በተራ ቁጥር 9 ላይ ያለ የንብረት ጨረታ። ዝርዝር መግለጫ በሰነዱ ላይ ይገኛል።

2. የጨረታ ተሳታፊነት መስፈርቶች

መስፈርት ዝርዝር
እምነት መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር፣ ተወዳዳሪው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆን አለበት።
ማስረጃ ከሚገለገልበት ደብር የድጋፍ ደብዳቤና የአባልነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችል።

ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች

ለተጫራቹ ዓይነት የሚቀርበው ሰነድ (ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር)
ነጋዴ ከሆነ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ።
ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ።
የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ።
የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ።

3. የጨረታው ሂደትና ቀነ-ገደብ

ክንውን ዝርዝር
የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ የማይመለስ 500.00 ብር (አምስት መቶ ብር)
ሰነድ የሚገዛበትና ንብረቱ የሚታይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ።
የንብረት ዕይታ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት።
መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
መክፈቻ ቀንና ሰዓት ከተዘጋበት ቀን በማግስቱ (በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በድርጅቱ ጽ/ቤት።
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ለእያንዳንዱ ክፍል የሚሆን ብር 5,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማስያዝ።
የውሃና መብራት ክፍያ አሸናፊው ከተረከበ በኋላ ራሱ ይከፍላል።
ንዑስ ኪራይ ቤቱን ከፋፍሎ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም
መነሻ ዋጋ ዝርዝር መነሻ ዋጋና መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ይገኛል።

4. አድራሻና መረጃ

ዓላማ ዝርዝር
ሰነድ የሚገዛበትና ማስገቢያ ቦታ የድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን።
የመክፈቻ ቦታ በድርጅቱ ጽ/ቤት።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0111-56-63-78
ሌላ መረጃ በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ።

ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.