Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ሐራጅ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች

Now Open
  • Viewed - 373

ሐራጅ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች

Now Open
  • Viewed - 373

Description

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር

 

ተራ ቁ. የተበዳሪ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ሰሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪ አይነት የስሪት ዘመን ሐራጅ መነሻ ዋጋ (ተ.ዕ.ታን ሳይጨምር) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1 ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ መሐል አራዳ አአ-03-A53273 አነስተኛ የሕዝብ- ኮሪያ ሀዩንዳይ 2014 እ.አ.አ. 1,530,000.00 ብር ኅዳር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
2 አቶ ፀጋ አዱኛ መስፍን / ወይ/ በረከት ዘሪሁን ምንዳዬ ሀዋሳ አአ-02-C19382 አውቶሞቢል – ህንድ-ሱዙኪ 2021 እ.አ.አ. 1,625,625.00 ብር ኅዳር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

 

2. የሐራጅ ደንቦችና አፈፃፀም

 

ገጽታ ደንብ
የጨረታ ማስያዣ የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4)ሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የሲፒኦ (C.P.O.) ብቻ ማስያዝ። ከሲፒኦ ውጪ የሚቀርብ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
የሐራጁ ቦታ የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ።
ምዝገባ የተጫራቾች ምዝገባ የሚደረገው ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ነው።
የመገኘት መብት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ በሐራጅ ላይ መገኘት ይችላሉ።
መታወቂያ ተጫራቾች መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል።
ለህጋዊ አካላት የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ስልጣንን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
የመክፈያ ጊዜ አሸናፊው ቀሪ ገንዘቡን በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለበት።
ያለመክፈል ቅጣት በ15 ቀናት ውስጥ ካልከፈለ፣ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል
ለተሸናፊዎች ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል
የግብር ክፍያዎች የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።
የመሰረዝ መብት ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. ለተጨማሪ መረጃ እና ንብረት መጎብኘት

 

  • ተሽከርካሪዎቹን ለመጎብኘት:
    • ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።
  • ለተጨማሪ መረጃ:
    • የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114 70 03 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.