ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቡባ/ፋማዳ/ሽጨ/017(2025/26)
ቡና ባንክ አ.ማ. ሲገለገልባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ሞዴል ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ማስታወቂያ ፣
| ተ.ቁ. |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሸከርካሪው ዓይነት |
የምርት ዘመን |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (ከተ.እ.ታ በፊት) |
ተሸከርካሪው የሚገኝበት ቦታ |
| 1 |
A.A-3-A56335 |
Hyundai Grand i10 |
2017 |
1,955,000.00 |
ቃሊቲ ቡና ኢንሹራንስ ሪከቨሪ ሳይት ጀርባ በሚገኘው የባንኩ መጋዘነ |
| 2 |
A.A-3-A02892 |
Nissan X-Trial |
2013 |
1,650,000.00 |
| 3 |
A.A-3-A15045 |
Toyota Avanza |
2014 |
2,380,000.00 |
| 4 |
A.A-3-A25946 |
Toyota Avanza * |
2015 |
2,325,000.00 |
| 5 |
A.A-3-A56354 |
Hyundai Grand i10 |
2017 |
1,955,000.00 |
ባህር ዳር ዲስትሪክት |
| 6 |
A.A-3-A14983 |
Toyota Avanza |
2014 |
2,380,000.00 |
ጎንደር ቅርንጫፍ |
| 7 |
A.A-3-A15523 |
Toyota Avanza |
2014 |
2,380,000.00 |
ብቸና ቅርንጫፍ |
| 8 |
A.A-3-A26149 |
Toyota Avanza |
2015 |
2,325,000.00 |
ድሬዳዋ ቅርንጫፍ |
| 9 |
A.A-3-A56373 |
Hyundai Grand i10 |
2017 |
1,955,000.00 |
አዳማ ዲስትሪክት |
የትራንስሚሽን እድሳት የሚፈልግ
የጨረታ ሰነዱ መግለጫዎች
- ተሸከርካሪዎችን መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ወሎ ሰፈር አደባባይ ጋራድ ህንፃ B(ቢ.)ታወር 7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ሎጂስቲክስ ዋና ክፍል ቢሮ ወይም በዝርዝሩ ላይ በተጠቀሱት የባንኩ ዲስትሪክቶች ወይም ቅርንጫፎች በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ ወይም የባንኩን የዲጅታል አማራጮች በመጠቀም በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ ገቢ በማድረግ እና ገቢ የተደረገበትን
ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ፡-
- በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙት ተሸከርካሪዎች በባንኩ ሎጂስቲክስ ዋና ክፍል ፣
- ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙት ተሸከርካሪዎች ከተጠቀሱት የባንኩ ዲስትሪክቶች ወይም ቅርንጫፎች ፣ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ፡-
2.1. በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙት ተሸከርካሪዎች በባንኩ ሎጂስቲክስ ዋና
ክፍል ፣
2.2. ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙት ተሸከርካሪዎች ከተጠቀሱት የባንኩ
ዲስትሪክቶች ወይም ቅርንጫፎች ፣ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ
አለባቸው፡፡ የጨረታው ሳጥን በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ
በ5፡00 ሰዓት ጋራድ ህንፃ B(ቢ.)ታወር 7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በባንኩ
ሎጂስቲክስ ዋና ክፍል ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የውጭ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻውን 10% እና የውስጥ ተጫራቾች 5% በቡና ባንክ አ.ማ. ወይም “Bunna Bank s.c. ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ካሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ፤ የጨረታው አሸናፊ ባሸነፉበት ዋጋ እና የመንገድ ትራንስፖርት በሚገምተው የተሸከርካሪዎቹ ግምት ልዩነት ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የጨረታው አሸናፊ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ በመሆን ለሚገዙት ተሸከርካሪ ክሊራንስ ለማውጣት ለመንገድ ትራንስፖርት የማስገመቻ ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ክፍያ በመፈፀም ተሸከርካሪውን ከባንኩ መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ተደርጎ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
- ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስየዙትን ገንዘብ የጨረታው ውጤት በተገለፀ ከአምስት ቀናት በኋላ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከላይ በተገለፁት ቦታዎች በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 011-557-72-91/011-126-43-67/011-126-19-01 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ