Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

Description

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸዉ ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

1. በሐራጅ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ. የተበዳሪ ስም ንብረት የሚገኝበት አድራሻ የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጅ ቀንና ሰዓት (2018 ዓ.ም)
1 አቶ አቡሳድ ነሻ አህመድ አዳማ ከተማ፣ ቀበሌ 03 1709 መጋዘን 17,183,808.00 ኀዳር 16፣ 5፡00 – 6፡00
2 ወ/ሮ ሶፋ መሃመድ የሻው ሸገር ከተማ፣ ገላን ክ/ከተማ 5000 ማኑፋክቸሪንግ (2 መጋዘኖች) እና ቢሮ (G+1) 64,916,824.00 ኅዳር 19፣ 5፡00 – 6፡00
3 አቶ ሀንፈሬ መሀመድ ኢሴ ሎጊያ ከተማ፣ ቀበሌ — 1680 መኖሪያ 596,248.00 ኅዳር 19፣ 5፡00 – 6፡00
4 አቶ ደመላሽ አድማስ ታምር ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ GN 5000 ግንባታ ላይ ያለ መጋዘን 11,465,757.00 ኅዳር 22፣ 5፡00 – 6፡00
5 አዱራ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ/ ጋምቤላ ከተማ፣ ቀበሌ 01 1434 ንግድ 9,026,345.00 ኅዳር 23፣ 5፡00 – 6፡00
6 ወይ/ መዓዛ አለማየሁ ካሳዬ ጋምቤላ ከተማ፣ ቀቤለ 05 600 መኖሪያ 5,920,927.00 ኅዳር 23፣ 8፡00 – 9፡00
7 ወይ/ ኩብራ ታጁ ሀሰን ወልቂጤ ከተማ 198.887 መኖሪያ 1,361,603.00 ኅዳር 23፣ 8፡00 – 9፡00
8 አቶ ያረጋል አጥናፍ ከበደ ምዕራብ ጎጃም፣ ቡሬ ከተማ፣ ቀበሌ 03 1000 ማኑፋቸቸሪንግ ግንባታ 2,566,262.00 ኅዳር 23፣ 5፡00 – 6፡00

 

2. የሐራጅ ደንቦች እና መስፈርቶች

 

 

ሀ. የጨረታ ማስያዣ (Bid Security)

 

  • የማስያዣ መጠን: የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ)
  • የማስያዣ ዓይነት: በሕብረት ባንክ አ.ማ. ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ። ከሲ.ፒ.ኦ. ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።

 

ለ. የሐራጅ መካሄጃ ቦታዎች

 

  • ንብረት ቁጥር 1-7: ሐራጁ የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው
  • ንብረት ቁጥር 8: ጨረታው የሚካሄደው ባህርዳር ከተማ፣ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና (ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ነው። (ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት)።

 

ሐ. የብድር ማመቻቸት

 

  • ብድር የሚሰጥባቸው ንብረቶች: ከተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተመለከቱትን ንብረቶች ብቻ።
  • የብድር መጠን: የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች፣ በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50% (ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል

 

መ. የክፍያ እና የውል ግዴታዎች

 

  • የምዝገባ ጊዜ: የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
  • ክፍያ እና ንብረት ዝውውር: ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ባንኩ ዋጋውን ሲቀበለው፣ ቀሪውን ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል ደብዳቤ ይሰጠዋል።
  • ቅጣት: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፤ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል
  • የአሸናፊ ግዴታ: የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።

 

ሠ. ተሳታፊነት እና ጉብኝት

 

  • ተሳታፊነት: በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው። ተጫራቾች መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል።
  • ድርጅቶች: የሕግ ሰውነት ያላቸው አካላት የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (ወይም ውክልና) ይዞ መቅረብ አለበት።
  • ንብረት ጉብኝት: የሚፈልግ ተጫራች ከሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።

 

3. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥሮች

 

ቅርንጫፍ/መምሪያ ስልክ ቁጥር
ሕብር ታወር ቅርንጫፍ 0115 57 54 47
ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 0114 71 40 78/91
ሎጊያ ሰመራ ቅርንጫፍ 0335 50 00 15
ቦምብ ተራ ቅርንጫፍ 0112 78 17 28/27
ባሮ ማዶ ቅርንጫፍ 0574 41 04 92
ጋምቤላ ቅርንጫፍ 0475 51 08 28
ወልቂጤ ቅርንጫፍ 0113 65 92 51
ቡሬ ቅርንጫፍ 0587 74 05 04
የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ 0114 70 03 15/47

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.