Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

በመጋዘን ውስጥ ተከማችተዉ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩ ልዩ ማሸጊያ ካርቶኖች እና ፕላስቲክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ

Now Open
  • Viewed - 76

በመጋዘን ውስጥ ተከማችተዉ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩ ልዩ ማሸጊያ ካርቶኖች እና ፕላስቲክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ

Now Open
  • Viewed - 76

Description

ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ  በመጋዘን ውስጥ ተከማችተዉ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩ ልዩ ማሸጊያ ካርቶኖች እና ፕላስቲክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

📦 ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ፡ ያገለገሉ ማሸጊያዎች ሽያጭ

 

 

📅 የጨረታ ቀናት

 

  • ማስታወቂያ የወጣበት ቀን: ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም (ማለትም ህዳር 9፣ 2025 ዓ.ም.)
  • ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት: ሐሙስ ህዳር 11 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • ጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት: ሐሙስ ህዳር 11 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡15 ሰዓት

 

📋 ለሽያጭ የቀረቡ የእቃ አይነቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የእቃ አይነቶች ዝርዝር መለኪያ ብዛት
1 የተለያዩ ማሸጊያ ካርቶኖች (የድርጅቱን ብራንድ የያዙ) በኪሎ 40,000.00
2 የተለያዩ አይነት የፕላስቲክ እቃዎች (የድርጅቱን ብራንድ የያዙ) በኪሎ 7,000.00
3 የሳኒታይዘር ማሸጊያ ጃር ከነ ክዳኑ 50cc በፍሬ 648,912.00
4 የሳኒታይዘር ማሸጊያ ጃር ከነ ክዳኑ 100cc በፍሬ 1,368,735.00
5 የሳኒታይዘር ማሸጊያ ጃር ከነ ክዳኑ 500cc በፍሬ 199,973.00

 

✅ የግዴታ መስፈርቶች (ለተጫራቾች)

 

  1. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
    • የጠቅላላ ዋጋዉን ሁለት ፐርሰንት (2%) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ “ኢስት አፍሪካ ላየን ብራንድስ አ.ማ” (East Africa Lion Brands Manufacturing SC) በሚል የአካዉንት ስም ገቢ ተደርጎ መቅረብ አለበት።
  2. የንግድ ፈቃድና ታክስ ሰርተፍኬት:
    • የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፍኬት) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ግዢ:
    • ድርጅቱ ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በ500 (አምስት መቶ) ብር በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል
  4. ተጨማሪ የፍቃድ መስፈርት (ለተ.ቁ 1 እና 2):
    • በተራ ቁጥር 1 (ካርቶን) እና 2 (ፕላስቲክ) ላይ ለመጫረት፣ ተጫራቾች ካርቶን የማምረት ፍቃድ እና ፕላስቲክ የማምረት ፍቃድ ያላችዉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
    • ይህንን የሚገልፅ ፍቃድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ።
    • የብራንድ ግዴታ: እቃዎቹ የድርጅቱን ብራንድ የያዙ ስለሆኑ ተጫራቾች ፈጭተዉ ለመጠቀም ግዴታ ይገባሉ እንዲሁም የሽያጭ ዉል ላይ የብራንድ ስሙን ላለመጠቀም ግዴታ ይገባሉ።

 

📍 አድራሻ እና የእውቂያ መረጃ

 

  • ጨረታ መክፈቻ ቦታ: የኢስት አፍሪካ ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ማህበር መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ
  • አድራሻ: ቢሾፍቱ ወረዳ ዲባዩ ቀበሌ ደካ ቦራ
  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥሮች: 0926260203 / 0962810807

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.