Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ከወይራ የተዘጋጀ የፀጉር ቅባት 397 gram ግዢ (በመደብ-1)፣ የልብስ ሣሙና (250 gm) ግዢ (በመደብ-2) እና የአልትራሳውንድ መሳሪያ  ግዢ (በመደብ-3) በግልፅ ጨረታ ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ  በኘሮጀክቱ ለሚገኙ ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች እና ለጤና ጣቢያ መግዛት ይፈልጋል

Now Open
  • Viewed - 73

ከወይራ የተዘጋጀ የፀጉር ቅባት 397 gram ግዢ (በመደብ-1)፣ የልብስ ሣሙና (250 gm) ግዢ (በመደብ-2) እና የአልትራሳውንድ መሳሪያ  ግዢ (በመደብ-3) በግልፅ ጨረታ ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ  በኘሮጀክቱ ለሚገኙ ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች እና ለጤና ጣቢያ መግዛት ይፈልጋል

Now Open
  • Viewed - 73

Description

ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ  መንግሥታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን መንግሥት ባወጣው የዳግም ምዝገባ ሥርዓት አጠናቆ በሰርተፊኬት ቁጥር 1135 በመመዝገብ በመላው ኢትዮጵያ በበጐ አድራጐት ሥራ ላይ (ንዲቀሳቀስ  የተፈቀደለት ድርጅት ነው፡: በዚሁም መሠረት ድርጅቱ በሚከተሉት መደቦች ማለትም ከወይራ የተዘጋጀ የፀጉር ቅባት 397 gram ግዢ (በመደብ-1)፣ የልብስ ሣሙና (250 gm) ግዢ (በመደብ-2) እና የአልትራሳውንድ መሳሪያ  ግዢ (በመደብ-3) በግልፅ ጨረታ ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ  በኘሮጀክቱ ለሚገኙ ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች እና ለጤና ጣቢያ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች እንድትሣተፉ ይጋብዛል፡፡

1. የሚፈለጉት ዕቃዎች እና ብዛት

ድርጅቱ በሶስት መደቦች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

መደብ ዝርዝር ዕቃ ዝርዝር መግለጫ (Specifications) መለኪያ ብዛት
መደብ 1 ከወይራ የተዘጋጀ የፀጉር ቅባት (Hair Oil) Semi-solid, olive oil–based pomade (ጭቃ ቅባት)፣ 1ኛ ደረጃ ጥራት፣ ብራንድ DAX Olive Oil ወይም ተመጣጣኝ። የተጣራ ክብደት: 397 gram. በቁጥር 5,042
መደብ 2 የልብስ ሣሙና (Laundry Soap) 250 gm በቁጥር 46,772
መደብ 3 የአልትራሳውንድ መሳሪያ (Ultrasound Machine) ዝቅተኛ መስፈርት፡ ተንቀሳቃሽ ላፕቶፕ አይነት፣ ለምርመራ ኢሜጂንግ የሚያገለግል፣ ሁለት (2) ፕሮቦች ያሉት። በቁጥር 2

2. የጨረታው የጊዜ ሰሌዳ እና አድራሻዎች

ክንውን ቀን (ከሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ) ሰዓት ቦታ / አድራሻ
የጨረታው መውጣት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜ ጥቅምት 19/2018 እስከ ጥቅምት 27/2018 (7 የስራ ቀናት) ጠዋት 2፡30 – 6፡00 እና ከሰዓት በኋላ 7፡00 – 10፡00 ዋናው መ/ቤት ፋይናንስ ክፍል
የጨረታ መዝጊያ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሠዓት ልደታ ፕሮጀክት አዳራሽ
የጨረታ መክፈቻ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሠዓት ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ ልደታ ፕሮጀክት (ኮሪያ ት/ቤት) ከልደታ ቤ/ክ በስተጀርባ ያለው አዳራሽ

3. ለተጫራቾች የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

ሀ. ህጋዊ መስፈርቶች

ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ፣ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡-

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ (በዘርፉ)።
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)።
  4. የዘመኑን ግብር ስለመክፈል ማረጋገጫ (Tax Clearance)።
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት።

ለ. የፋይናንስና የቴክኒክ መስፈርቶች

  1. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO): ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ በድርጅቱ ስም ማሰራት።
  2. የሃሳብ አቀራረብ፡ የመወዳደሪያ ሃሳብዎን (ዋጋ/Financial) እና (ቴክኒክ/Technical) ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በመለየት በሁለት ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት።
  3. ናሙና፡ ለአልትራሳውንድ በስተቀር ለሁሉም ቁሳቁሶች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው።

ሐ. የአቅርቦት ሁኔታዎች

  1. የማስረከቢያ ጊዜ: ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ።
  2. የማስረከቢያ ቦታ: አንጐለላ እና ወልቂጤ (ትራንስፖርት በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል)።
  3. የሰነድ መግዣ ዋጋ: የማይመለስ 600.00 ብር (ስድስት መቶ ብር)

4. አድራሻዎች እና መረጃ

ዓላማ አድራሻ
ሰነዱ የሚሸጥበት (ዋናው መ/ቤት) ልደታ ክ/ከተማ፣ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ፣ አህመድ የገበያ ማዕከል 5ኛ ፎቅ (ፋይናንስ ክፍል)።
ጨረታው የሚከፈትበትና ናሙና የሚሰጥበት ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ ልደታ ፕሮጀክት (ኮሪያ ት/ቤት) ከልደታ ቤ/ክ በስተጀርባ ያለው አዳራሽ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251-115578614, +251-115575889

ማሳሰቢያ: ናሙናዎች ጨረታው ከተከፈተ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ መወሰድ አለባቸው፤ ከዚያ በኋላ ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም። ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.