Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የሐራጅ ማስታወቂያ

Now Open
  • Viewed - 19

የሐራጅ ማስታወቂያ

Now Open
  • Viewed - 19

Description

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – የሐራጅ ማስታወቂያ

ባንኩ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን እና ከዚህ በታች የተመለከተውን የጭነት ተሽከርካሪና ተሳቢ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ይሸጣል።

1. የሐራጅ ንብረት ዝርዝር

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረቱ ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የሐራጅ መነሻ ዋጋ የሐራጅ ቀንና ሰዓት
1 ኳድራንት አፓርል ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማ የጭነት መኪና እና ተሳቢ (Trailer) ኢት-03-66900 እና ኢት-03-20264 በሰነዱ ላይ የተገለጸው መጋቢት 15/2018 (ጠዋት 3፡00-4፡00)
  • ተጨማሪ የቴክኒክ መረጃ፡

    • የሞተር ቁጥር፡ F3BEE681GB220222647

    • የሻንሲ ቁጥር፡ WjMETRE8EC286633 እና TT-1044-14

    • የተመረተበት ዓመት፡ 2014 (እ.ኤ.አ)


2. ዋና ዋና የሐራጅ ደንቦች

  • የመጫረቻ ቅድመ ሁኔታ (CPO)፦ ተጫራቾች የመነሻ ዋጋውን አንድ አራተኛ (1/4) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CPO ማቅረብ ተመራጭ ነው።

  • የሐራጅ ቦታ፦ ባህር ዳር ከተማ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቅጥር ጊቢ ውስጥ።

  • ሕጋዊ ሰነዶች፦ የንግድ ማህበርን ወክሎ የሚጫረት አካል የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የመግዛት ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለበት።

  • ተጨማሪ ክፍያዎች፦ አሸናፊው ተጫራች በሽያጩ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የመንግስት ግብር እና ከስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።

  • የክፍያ ሁኔታ፦ አሸናፊው ቀሪውን ክፍያ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም።


3. ምልከታና ተጨማሪ መረጃ

  • ምልከታ፦ ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ አካላት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻው ፕሮግራም መሠረት መጎብኘት ይችላሉ።

  • ስልክ ቁጥር፦ 011 113 05 08

  • አድራሻ፦ አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት፣ 42ኛ ፎቅ፣ ፎርክሎዠር (Foreclosure) ክፍል።


ማሳሰቢያ፦ ንብረቱን ያሸነፈ አካል ክፍያውን በፈጸመ በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል። ባንኩ ሐራጁን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.