የተሽከርካሪዎች አጠቃላይ የኢንሹራንስ ሽፋን (Comprehensive Insurance) ግልጽ ጨረታ
ጄ ኤስ አይ (JSI Research & Training Institute, Inc.)
በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ላይ ለረጅም ዓመታት ስኬታማ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው ጄ ኤስ አይ (JSI)፣ ለድርጅቱ ተሽከርካሪዎች የሚሆን አጠቃላይ የኢንሹራንስ ሽፋን (Comprehensive Insurance Coverage) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
ሕጋዊ ሰነዶች፦ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) እና የቲን (TIN) ምዝገባ ሰርተፍኬቶች።
-
የሰነድ አቀራረብ፦ የቴክኒክ እና የፋይናንሻል ሰነዶች በሁለት ለየብቻ በታሸጉ ፖስታዎች ከነኮፒያቸው (Original & Copy) መቅረብ አለባቸው።
-
የዋጋ ጸናታ፦ የቀረበው የዋጋ ዝርዝር ጨረታው ከገባበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ 30 ተከታታይ ቀናት የጸና መሆን አለበት።
2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና መዝጊያ ቀን
-
የሰነድ መገኛ፦ ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን (RFQ) ከመጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (March 30, 2026) ጀምሮ ከጄ ኤስ አይ ዋና መሥሪያ ቤት መውሰድ ይችላሉ።
-
የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም (April 06, 2026) እስከ ቀኑ 10:30 (04:30 PM) ሰዓት።
-
የመክፈቻ ጊዜ፦ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም (April 07, 2026) ጠዋት 5:00 (11:00 AM) በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት።
3. አድራሻ እና መገናኛ