Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የውጭ ኦዲት አገልግሎት ዳግም ጨረታ ማስታወቂያ (Re-Advertisement)

Now Open
  • Viewed - 14

የውጭ ኦዲት አገልግሎት ዳግም ጨረታ ማስታወቂያ (Re-Advertisement)

Now Open
  • Viewed - 14

Description

የውጭ ኦዲት አገልግሎት ዳግም ጨረታ ማስታወቂያ (Re-Advertisement)

የጨረታ መለያ ቁጥር፦ HCSC/NCB/0003/2018

ሀበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ለተከታታይ ሦስት ዓመታት (እ.ኤ.አ ከታኅሳስ 31፣ 2025 ጀምሮ) የኩባንያውን የፋይናንስ መግለጫዎች ኦዲት የሚያደርግ ገለልተኛ የውጭ ኦዲተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

1. የሥራው ዓላማ (Objective)

አሸናፊው የኦዲት ተቋም የኩባንያውን የፋይናንስ መግለጫዎች በመመርመር ገለልተኛ የሙያ አስተያየት የመስጠት እና የኩባንያው ሀብቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል።


2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  • ሕጋዊ ፈቃድ፦ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የሕዝብ ኦዲተር (Public Auditor) ተብሎ የተመዘገበ እና ፈቃድ ያለው።

  • የሥራ ልምድ፦ በኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች እና በማኑፋክቸሪንግ (ማምረቻ) ኩባንያዎች ኦዲት ላይ በቂ ልምድ ያለው።

  • ዕውቀት፦ ስለ ሀገሪቱ ሕጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች በቂ ዕውቀት ያለው።

  • ሰነዶች፦ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) ምዝገባ፣ የቲን (TIN) ቁጥር እና ወቅታዊ የግብር ክሊራንስ።


3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና አቀራረብ

  • የሰነድ አወሳሰድ፦መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም (March 18, 2026) ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት መግዛት ይቻላል።

  • የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም (April 1, 2026) ከጠዋቱ 4:00 (10:00 AM) ሰዓት።

  • የመክፈቻ ጊዜ፦ በዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 (10:30 AM) ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት።


4. አድራሻ እና መገናኛ

  • ቦታ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01፣ ጌታስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ (GetAs International Bldg) 7ኛ ፎቅ፣ ቸርችል ጎዳና ዝቅ ብሎ (ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ጀርባ)።

  • ኢሜይል፦ melakug@habeshacement.com ወይም hanaa@habehshacement.com

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.