Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 402

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 402

Description

ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ እንዳልካቸው ደመላሽ ነጋ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም የንብረቱ መገኛ አድራሻ የንብረቱ አይነት/አገልግሎት መነሻ ግምት (ብር)
1 እንዳልካቸው ደመላሽ / ዓለማየሁ ጎነጠ አብክመ ጎንደር ከተማ፣ አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 20 ኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል የድርጅት ቤት 37,413,186.11
2 እንዳልካቸው ደመላሽ / ስዩም አብርሃ አዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 መኖሪያ ቤት (B1+G+G2 ዋና እና B1+G ሰርቪስ) 19,763,287.53

 

የጨረታው ቀን እና ቦታ

 

ተ.ቁ ንብረት የጨረታ ቀን ሰዓት ቦታ
1 የኢንዱስትሪ ቤት (ጎንደር) ህዳር 20/2018 ዓ.ም 3፡00-6፡00 ጠዋት ጎንደር ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ሕንጻ ላይ
2 መኖሪያ ቤት (አ.አ) ህዳር 20/2018 ዓ.ም 3፡00-6፡00 ጠዋት አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋናው መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ላይ

 

2. የጨረታ ደንቦች እና ቅድመ ሁኔታዎች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ: ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ህጋዊ አካላት: በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል።
  3. የአሸናፊነት ማረጋገጫ: የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ነው።
  4. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ዋጋውን አጠቃሎ መክፈልና ንብረቱን መረከብ አለበት።
    • በ15 ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
    • ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
  5. ግብር እና ወጪዎች: የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ ቫት የሚከፈል ከሆነ፣ እና ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውም ወጪዎች ይሸፍናል።
  6. የሊዝ ክፍያ: ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ፣ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል
  7. ንብረት መጎብኘት: ተጫራቾች ቤቶቹን ሕዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ
  8. የባንኩ መብት: ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ

 

  • ስልክ ቁጥር: 0918303144
  • ድርጅት: ፀደይ ባንክ አ.ማ.

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.