Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

Description

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተራ ቁ. የተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ (ከተማ/ክፍለ ከተማ/ወረዳ) የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የንብረት አይነት የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1 ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ ሸገር አዲስ አበባ፣ አራዳ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09 852.6 በግንባታ ላይ ያለ ሕንፃ (ለድርጅት አገልግሎት) 355,897,544.00 ኅዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከ5፡00 እስከ 6፡00 ጠዋት
2 አቶ ተሰማ አያኖ ሻመና ለቡ ላፍቶ አዲስ አበባ፣ ንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 01 175 ለመኖሪያ የሆነ ቤት 20,346,579.00 ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከ5:00 እስከ 6:00 ጠዋት
3 አቶ ጁሀር ሰይድ እንድሪስ ጎላ ሰፈር አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 48.87 ለመኖሪያ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት 2,632,133.00 ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከ5:00 እስከ 6:00 ጠዋት
4 አቶ አበራ ገብሬ ብርሃኑ ወልድያ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ወልድያ ከተማ፣ ቀበሌ 03 150 ለመኖሪያ የሆነ ቤት 1,688,620.00 ታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከ5:00 እስከ 6:00 ጠዋት
5 አቶ ረሻድ አህመድ በሽር / አቶ ኑርሰፋ ኢብራሂም ወልቂጤ ወልቂጤ ከተማ፣ ጉብሬ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 01 250 ለንግድ የሚውል ቤት 1,747,345.00 ታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከ5፡00 እስከ 6፡00 ጠዋት
6 አቶ መኳንንት ታደሰ ረዳ ባህርዳር ባህርዳር ከተማ፣ አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ 728 ለመኖሪያ የሆነ ቤት 18,035,600.00 ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከ5፡00 እስከ 6፡00 ጠዋት

 

2. የሐራጅ መካሄጃ ቦታዎች

 

ተራ ቁ. የንብረት አድራሻ ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ
1 – 3 አዲስ አበባ ንብረቶች የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ።
4 – 5 ወልድያ እና ወልቂጤ ንብረቶች ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ይካሄዳል።
6 ባህርዳር ንብረት ባህርዳር ከተማ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና (ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ።

 

3. የሐራጅ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (ሲ.ፒ.ኦ):
    • ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ)ሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
    • ከሲ.ፒ.ኦ. ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም
  2. ክፍያ እና ቅጣት:
    • ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ዋጋው በባንኩ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት።
    • በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ፣ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፤ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነትም ይጠየቃል
    • ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል
  3. ግብር እና ወጪዎች:
    • የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል
  4. መገኘት:
    • በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾችተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው
    • ተጫራቾች ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል
    • የሕግ ሰውነት ያላቸው አካላት ሲሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በፀደቀ መመስረቻ ጽሑፍ/ቃለ ጉባኤ/ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
  5. ምዝገባ:
    • የተጫራቾች ምዝገባ የሚደረገው ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ነው
  6. ንብረት መጎብኘት:
    • ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።
  7. የባንኩ መብት:
    • ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

4. የእውቂያ መረጃ (ለተጨማሪ መረጃ)

 

ቅርንጫፍ ስልክ ቁጥር
ሸገር ቅርንጫፍ 011 1 26 54 62
ለቡ ላፍቶ ቅርንጫፍ 0114 19 90 61
ጎላ ሰፈር ቅርንጫፍ 0111 26 22 07
ወልድያ ቅርንጫፍ 0333 31 20 21 / 20
ወልቂጤ ቅርንጫፍ 0113 65 85 27
የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ (ዋናው መስሪያ ቤት) 0114 70 03 15 / 47

 

 

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.