Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልፅ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 427

ግልፅ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 427

Description

ፀደይ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ የንብረት አይነት ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)
1 ወ/ሮ አስቴር በቀለ/ አቶ አወቀ ወርቁ ሚዳ ለመኖሪያ ቤት መራኛ ከተማ 250 1,131,591.14
2 ሀበሻ ኢንጅነሪንግና አርክቴክቸራል ኃ/የተ/የግል ማህበር/ አቶ ግሩም መኮንን ጠባሴ ለኢንዲስትሪ (ኮርጌትድ ቦርድ) ደ/ብርሃን ከተማ ቀበሌ 08 7,000 17,161,534.61

 

የጨረታው ጊዜ እና ቦታ

 

ተ.ቁ ቀን ሰዓት
1 ህዳር 20/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00
2 ህዳር 20/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 እስከ 7፡00
  • የሐራጁ ቦታ: ፀደይ ባንክ ደ/ብርሃን ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ

 

2. የሐራጁ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ:
    • ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በፀደይ ባንክ አ.ማ. ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
  2. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል አለበት።
    • ካልከፈለ ሐራጁ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል
  3. ግብር እና ወጪዎች:
    • የሀራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ የሊዝ ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ፣ እና ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ ሌሎች ወጪዎችን ገዢው ይከፍላል
  4. ንብረት መረከብ: ገዢው የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረከብ አለበት። በተጠቀሰው ጊዜ ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
  5. መታወቂያ/ውክልና:
    • ተጫራቾች ለመጫረት ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣ ፓስፖርት ወይም ብሔራዊ መታወቂያ) መያዝ አለባቸው።
    • የህግ ሰውነት ያላቸው አካላት ደግሞ ዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ስልጣኑን የሚያሳይ ሰነድ (የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ/ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ) ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  6. ንብረት መጎብኘት: ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከአበዳሪው ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላል።
  7. የባንኩ መብት: ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ

 

  • ስልክ ቁጥር: $\text{0116812313}$ (በሥራ ሰዓት)
  • ድርጅት: ፀደይ ባንክ አ.ማ.

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.