Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 340

ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 340

Description

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የሐራጅ ማስታወቂያ፡ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.

 

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት፣ ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች (ቤቶች እና ተሽከርካሪዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ ነው።


 

ሀ. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ (ቤት)

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የንብረቱ ዓይነት የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት
1 አቶ ገብረሂወት ከበደ የዕብዮ የጭላ የጭላ ከተማ፣ ወረዳ/ቀበሌ – 250 መኖሪያ 1,252,650.27 ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ (በባንኩ የጭላ ቅርንጫፍ)

 

ለ. ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ (ቤቶች)

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የንብረቱ ዓይነት የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት
1 ዳንኤል ጌታቸው/ራዳር ኮንስትራክሽን/ የካ መቀሌ፣ ዓዲ ሓቂ 250 G+1 መኖሪያ ቤት 12,325,956.69 ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ (በመቀሌ ሰሜን/ግእዝ ሪጅን መስሪያ ቤት)
2 አቶ ብርሃነ ገ/መድህን / አቶ ገብረየሱስ ገ/መድህን ካዛንቺስ መቀሌ፣ ሰሜን 248 መኖሪያ ቤት 12,572,401.60 ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ (በመቀሌ ሰሜን/ግእዝ ሪጅን መስሪያ ቤት)
3 አቶ ሓዱሽ ተወልደብርሃን ገብረመስቀል ሰለኽለኻ መደባይ ዛና፣ ዓዲ ቀማልክ አንድ ሄክታር የኢንቨስትመንት ልማት የእንስሳት ማደለቢያ 2,421,806.72 ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ (በባንኩ ሰለኽለኻ ቅርንጫፍ)

 

ሐ. ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ (ተሽከርካሪዎች)

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ የመኪናው አይነት ሰሌዳ ቁጥር የተሰራበት ዓ.ም የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት
1 ዳንኤል ጌታቸው/ራዳር ኮንስትራክሽን/ የካ ገልባጭ ኢ.ት-03-77982 እ.ኤ.አ 2015 4,750,000 ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ (አዲስ አበባ ዋና መስሪያ ቤት)
2 አቶ ሙልጌታ ታደሰ(ማን ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ) መሳለሚያ ገልባጭ ኢ.ት-03-93946 እ.ኤ.አ 2017 4,000,000 ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ (አዲስ አበባ ዋና መስሪያ ቤት)

 

3. የጨረታ ደንቦች (ማሳሰቢያ)

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (ሲፒኦ):
    • ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25%አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ስም የተሰራ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. የጉምሩክ ቀረጥ/ታክስ (ተሽከርካሪዎች):
    • በተ.ቁ 1 ላይ ለተመለከተው ተሽከርካሪ ብር 200,134.24
    • በተ.ቁ 2 ላይ ለተመለከተው ተሽከርካሪ ብር 396,411.35
    • እስከ 07/02/2018 ዓ.ም ድረስ ያልተከፈለ የቀረጥ እና ታክስ ያለባቸው ሲሆን፣ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገቡ ክፍያዎች፣ ግብር/ቀረጥ ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው/ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል
  3. የምዝገባ ሰዓት:
    • ምዝገባ የሚከናወነው በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ 4፡00 – 5:30፣ በከሰዓቱ ደግሞ ከ 8፡00-9፡30 ድረስ ይሆናል።
    • ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን፣ አሸናፊው ካልተለየ ግን ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
  4. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታው አሸናፊ የሽያጩን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል።
    • በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ፣ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
    • የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል።
    • ለጨረታ የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል
  5. ንብረት ማስተላለፍ:
    • ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  6. ንብረት መጎብኘት:
    • ንብረቶችን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
  7. የባንኩ መብት:
    • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

4. የእውቂያ መረጃ

 

  • አዲስ አበባ ዋና መ/ቤት (ሕግ አገልግሎት መምሪያ): ስልክ ቁጥር 011-662-7120
  • ሰለኽለኻ ቅርንጫፍ (ለመደባይ ዛና ንብረት): ስልክ ቁጥር 0914492789
  • የጭላ ቅርንጫፍ (ለየጭላ ንብረት): ስልክ ቁጥር 0933371487

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.