ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፡ ዳሽን ባንክ አ.ማ. (የመኖሪያ ቤት ሽያጭ)
ዳሽን ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚከተለውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ አወዳድሮ ይሸጣል።
1. በሐራጅ የሚሸጥ ንብረት ዝርዝር
| ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የአስያዥ ስም |
ለጨረታው የቀረበው ንብረት |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) |
የጨረታው መነሻ ዋጋው (ብር) |
| 1 |
ናስር ራሺድ መሀሙድ |
ወ/ሮ ዘሀራ ሀዲ ሃሮሽ |
የመኖሪያ ቤት |
ጂግጅጋ ከተማ፣ ቀበሌ 16 |
400 |
2,201,017 |
የጨረታው መካሄጃ ጊዜ እና ቦታ
- ቀን: ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም
- ሰዓት: 4:00 – 6:00
- ቦታ: ጨረታው የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ነው።
2. የሐራጅ ደንቦች (ማሳሰቢያ)
- የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በዳሽን ባንክ አ.ማ. ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
- ምዝገባ:
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
- የሐራጅ አሸናፊነት ማረጋገጫ:
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ነው።
- ክፍያ እና ቅጣት:
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል።
- ባይከፍል፣ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም።
- በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ግብር እና ወጪዎች:
- የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር፣ ታክስ፣ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል።
- መገኘት:
- በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ባይገኙ ግን ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
- የሰዓት ማራዘም: ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠንቀቀ ሊራዘም ይችላል።
- የባንኩ መብት: ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
3. የእውቂያ መረጃ
- ስልክ ቁጥር: 0111-704038 ወይም 0111-704976
- ድርጅት: ዳሽን ባንክ አ.ማ.