🧾 ኦሳካ ብረታ ብረት ኃ/የተ/የግ/ማህበር: የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅቱ በአዋጅ ቁጥር 847/2014 እና በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 332/2014 መሠረት የሂሳብ ሥራውን በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ደረጃ (IFRS) ለመመዝገብ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ አካውንቲነግና ኦዲት ቦርድ (AABE) ባስቀመጠው መርሃግብር መሠረት ሥራውን ለመሥራት ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን በጨረታ ይጋብዛል።
📌 የሥራው ዝርዝር
-
ተፈላጊ ሥራ: የድርጅቱን የሂሳብ ሥራ በኢትዮጵያ አካውንቲነግና ኦዲት ቦርድ መርሃግብር መሠረት ወደ IFRS ደረጃ ማሸጋገር (Conversion) እና መመዝገብ።
-
የጨረታ ሂደት: የድርጅቱን ስፋትና የሂሳብ ደረጃ ከግምት ውስጥ ያስገባ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ማቅረብ ያስፈልጋል።
-
በመጀመሪያ የቴክኒካል ሃሳቡ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ይመረጣል።
-
በመቀጠልም የፋይናንስ ፕሮፖዛሉ ተከፍቶ አሸናፊው ይወሰናል።
-
ተፈላጊ የሥራ ፍጥነት: ሥራውን ባፋጣኝ ሠርቶ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይፈለጋሉ።
📜 በቴክኒካል ፕሮፖዛል መካተት ያለባቸው ዝርዝሮች
ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡
-
የህጋዊነት ማረጋገጫዎች (Renewed Licenses):
-
ወቅታዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት።
-
የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት።
-
የታደሰ የሞያ ምዝገባ ሰርተፊኬት (ከAABE ወይም ከሚመለከተው አካል)።
-
የድርጅት መረጃና ልምድ:
-
የመልካም አፈፃፀም ማረጋገጫ:
-
የአፈፃፀም ስልት:
📅 የሰነድ ማስረከቢያ ጊዜና አድራሻ
-
የመጨረሻ ቀን: ይህ ማስታወቂያ በመጨረሻ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰነዶቻችሁን እንድታቀርቡ ይፈለጋል።
-
አድራሻ: ብስራተ ገብርኤል ባይኔ ህንፃ 4ኛ ፎቅ
-
ስልክ ቁጥር: 0113203731 ፣ 0912341645