1. የጨረታው የጊዜ ሰሌዳ እና አጠቃላይ መረጃ
| ዝርዝር |
መረጃ |
| ድርጅት |
የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን |
| አገልግሎት |
የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት) |
| የጨረታ ማስረከቢያ ጊዜ |
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት |
| የጨረታ ማስረከቢያ ሰዓት |
በሥራ ሰዓት |
| የአቀራረብ ዘዴ |
በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፕሮፖዛል ማቅረብ |
| TOR |
የተዘጋጀውን TOR ከድርጅቱ መውሰድ ይቻላል። |
2. አስገዳጅ መመዘኛዎች
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል:
- የሙያ ፈቃድ: በኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ (AABE) ወይም እሱ በሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን።
- የንግድ ፈቃድ: በሀገሪቱ ህግ መሠረት ኦዲት ሥራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ: ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።
- የምርት ገበያ ምዝገባ: በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን (ECX) የተመዘገበና ማስረጃ ማያያዝ የሚችል።
- ተሞክሮ: ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ ምርመራ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት ኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ መሆን።
- የባለሙያ ብቃት: የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎች በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ።
3. የእውቂያ መረጃ
- አድራሻ: አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 በዩኒየኑ ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ
- ስልክ: 011 440 7165 እና 0911 40 9994
- ማሳሰቢያ: ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።