የህንፃ ኮርኒስ ሥራ (Ceiling Work) ግልጽ ጨረታ
ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማኅበር
ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማኅበር በማሳደስ ላይ ላለው ባለ አንድ ፎቅ (G+0) ህንፃ የኮርኒስ ሥራ ብቃት ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
ሕጋዊ ሰነዶች፦ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት።
-
ልምድና ግብዓት፦ በሥራው ላይ በቂ ልምድ ያላቸውና ለሥራው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችንና ማቴሪያሎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
-
ናሙና (Sample)፦ እያንዳንዱ ተጫራች የሚሠራበትን የማቴሪያል ዓይነት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።
-
ኃላፊነት፦ በሥራው ላይ ለሚደርስ ማንኛውም እንከንና ውድቀት ተቋራጩ ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና መዝጊያ ቀን
-
የሰነድ ዋጋ፦ የማይመለስ ብር 500.00።
-
የአከፋፈል ሁኔታ፦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000184750507 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን መያዝ ያስፈልጋል።
-
ሰነድ መገኛ፦ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1፣ ሸማ ተራ ህንፃ ላይ በሚገኘው ጊዜያዊ ቢሮ ከመጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (March 30, 2026) ጀምሮ።
-
የመዝጊያ ቀን፦ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም (May 02, 2026) ጠዋት 4:00 ሰዓት።
-
የመክፈቻ ጊዜ፦ በዕለቱ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም (May 02, 2026) ጠዋት 4:30 ሰዓት በነባር አ/ማ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት።
3. አድራሻ እና መገናኛ