Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የምግብ ዘይት  ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 351

የምግብ ዘይት  ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 351

Description

ራስ ጋይንት ሁለ/የገ/ህ/ስ//ማህበራት ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ በስሩ ለአሉ አባል መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር እና ለአካባቢዉ ለሚገኙ ማህብረሰብ ለምግብ አገልግሎት የሚዉል 80,000 (ሰማኒያ ሽህ) ሊትር ፈሳሽ የምግብ ዘይት   በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

🍽️ ራስ ጋይንት ዩኒዬን፡ የምግብ ዘይት ግዥ ግልፅ ጨረታ

 

📌 የግዥ ዝርዝር

 

የሚገዛው ዕቃ መጠን (ሊትር) መድረሻ ቦታ
ፈሳሽ የምግብ ዘይት 80,000 (ሰማኒያ ሽህ) የዩኒዬኑ መጋዘን (ነፋስ መውጫ ከተማ)

📅 የጨረታ ቀናት እና ሰዓቶች (2018 ዓ.ም.)

 

ተግባር ቀን (2018 ዓ.ም.) ሰዓት
የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ መጀመርያ 15/03/2018 ከጧቱ 2፡30
የጨረታ መዝጊያ 22/03/2018 ከቀኑ 9፡00 ሠዓት
የጨረታ መክፈቻ 22/03/2018 ከቀኑ 9፡30 ሠዓት

ማስታወሻ: ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

🏢 ሰነድ መውሰጃ እና ማስገቢያ ቦታ

 

  • አድራሻ: የዩኒዬኑ ቢሮ፣ ነፋስ መውጫ ከተማ

  • የጨረታ ሳጥን: በዩኒዬኑ ቢሮ፣ ነፋስ መውጫ ከተማ።

  • የሰነድ ማግኛ ዘዴ: በአካል በዩኒዬኑ ቢሮ በመቅረብ፣ ወይንም ተጫራቾች በሚያሳውቁት ኢሜል አድራሻ ወይም ቴሌግራም ይላካል።

📜 የብቃት እና የሰነድ መስፈርቶች

 

  1. የንግድ ፈቃድ:ምግብ ምርቶች ጅምላ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም በምግብ ዘይት ጅምላ ንግድ ፍቃድ ያለዉ/ያላቸዉ መሆን።

  2. ታክስ: የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

  3. ቲን: የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።

  4. የማስረከብ ወጪ: የምግብ ዘይቱ ምረት መረከቢያት ቦታ በዩኒዬኑ መጋዘን ሲሆን የማስጫኛ፣ የማውረጃ (ወዛደር ወጭ) እና የትራንስፖርት (የማጓጓዢያ) ወጭ በሻጭ (አቅራቢው) የሚሸፈን ይሆናል

💰 የፋይናንስ እና የጨረታ ማስያዣ

 

  • የጨረታ ሰነድ ዋጋ: የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር)።

  • የመክፈያ መንገድ: በራስ ጋይንት ዩኒዬን ስም በተከፈተዉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነፋስ መውጫ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር 1000025648106 ማስገባት።

  • የባንክ ደረሰኝ ማቅረብ: የባንክ ዲፖዚት እስሊፕ (ኦርጅናል) ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብሮ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ያስፈልጋል።

  • የጨረታ ማስከበሪያ (CPO): ከሞሉት የጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው በፖስታ ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

  • የሰነድ ማሸግ: ከብቃት ማስረጃዎች (ፎቶ ኮፒ)፣ ከባንክ ዲፖዚት እስሊፕ እና ከሲፒኦ ጋር ተያይዞ በታሸገ ፖስታ፣ ከፖስታው ላይ የተጫራቹን ሙሉ ስም እና አድራሻ በሚገልጽ ማህተም በማድረግ ማቅረብ።

📞 ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር

 

  • ስልክ ቁጥር: 0910138148 / 0918281450 / 0940431516

ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.