የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር እና ክትትል ሥራ (Integrated Pest Control) ጨረታ
ሮሚና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (Romina PLC) የጨረታ መለያ ቁጥር፦ 001/2018
ሮሚና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለሚያስተዳድራቸው ሬስቶራንቶች፣ ኬክ ቤቶች፣ ፋብሪካዎች እና መጋዘኖች የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር (Pest Control) ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
ሕጋዊ ሰነዶች፦ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የቫት (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት።
-
የብቃት ማረጋገጫ፦ በምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን (EFDA) የተሰጠ ወይም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
-
የሥራ ልምድ፦ በዘርፉ በሆቴሎችና ሬስቶራንቶች ላይ ቢያንስ የ5 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው።
-
አቀራረብ፦ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ፣ ማኅተም እና ፊርማ በማሳረፍ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ።
2. የጨረታ ሰነድ (TOR) አወሳሰድ እና አቀራረብ
-
የሰነድ መገኛ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 3፣ አውሮፓ ሕብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ኖህ ዲፕሎማት አፓርትመንት፤ የሮሚና ዋና ቢሮ (ግዥ አስተዳደር ወይም የምግብና መጠጥ ዳይሬክተር ቢሮ)።
-
የመዝጊያ ቀን፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ።
-
የመክፈቻ ጊዜ፦ ጨረታው በ10ኛው ቀን ተዘግቶ በ 11ኛው ቀን ይከፈታል።
3. ለበለጠ መረጃ
-
ስልክ ቁጥር 1፦ 0984-00-84-59
-
ስልክ ቁጥር 2፦ 0911-30-28-92