Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የትምህርት ቤቶች የውኃ አቅርቦት እና የእጅ መታጠቢያ ግንባታ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 11

የትምህርት ቤቶች የውኃ አቅርቦት እና የእጅ መታጠቢያ ግንባታ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 11

Description

የትምህርት ቤቶች የውኃ አቅርቦት እና የእጅ መታጠቢያ ግንባታ ጨረታ

 ካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ (TCC-E)

የጨረታ መለያ ቁጥር፦ NCB No. 008/2026 TCC-E

ካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትራኮማ በሽታን ለመከላከል የሚያገለግሉ የውኃ አቅርቦት እና የእጅና ፊት መታጠቢያ ተቋማት ግንባታን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ (NCB) አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

1. የሥራው ዝርዝር በምድብ (Lots)

ምድብ (Lot) የወረዳ ስም የሥራው ዓይነት (Scheme Type) የኮንትራክተር ደረጃ የግንባታ ጊዜ
Lot-1 ዳህና (Dahana) የምንጭ ልማት (Spring Development) WWC/GWWC-7 እና ከዚያ በላይ 60 ቀናት
2 ዳህና (Dahana) የጣራ ውኃ አሰባሰብ እና መስመር ዝርጋታ WWC/GWWC-7 እና ከዚያ በላይ 60 ቀናት
3 ሰቆጣ ዙሪያ የውኃ መስመር ዝርጋታ (Line Extension) WWC/GWWC-7 እና ከዚያ በላይ 30 ቀናት
4 ሰቆጣ ዙሪያ ጥልቀት የሌለው ጉድጓድ ቁፋሮ (Shallow Well) 5-In drilling እና WWC-7 60 ቀናት

2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  • ሕጋዊ ፈቃድ፦ በውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተሰጠ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የውኃ ሥራዎች ተቋራጭ (WWC-7/GWWC-7) እና ከዚያ በላይ።

  • ልዩ መስፈርት (Lot-4)፦ ለጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ (Shallow Well) 5-In drilling ፈቃድ ያለው።

  • ሰነዶች፦ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) ምዝገባ እና የ2018 በጀት ዓመት የግብር ክሊራንስ።


3. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)

  • መጠን፦ ለእያንዳንዱ ምድብ (Lot) የቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2%

  • ሁኔታ፦ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና።

  • የጸናበት ጊዜ፦ ቢያንስ ለ 120 ቀናት የጸና መሆን አለበት።


4. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና አቀራረብ

  • የሰነድ ዋጋ፦ ጨረታው በነፃ የሚሰጥ ሲሆን፣ ሰቆጣ በሚገኘው የካርተር ሴንተር ዞን ጽሕፈት ቤት ማግኘት ይቻላል።

  • የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (April 08, 2026) ጠዋት 4:00 (10:00 AM) ሰዓት።

  • የመክፈቻ ጊዜ፦ በዕለቱ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4:30 (10:30 AM) ተጫራቾች በተገኙበት።

  • አድራሻ፦ ሰቆጣ ከተማ፣ ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የካርተር ሴንተር ጽሕፈት ቤት።


5. መገናኛ ስልኮች

  • 0936 17 07 77 / 0977 56 25 11 / 0918 76 68 70 / 0912 74 95 56

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.