Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የዕቃዎች ግዥ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 20

የዕቃዎች ግዥ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 20

Description

ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት – የዕቃዎች ግዥ ጨረታ

ድርጅታችን ከቻይልድ ፈንድ (ChildFund) ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማጠናከር እና ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. የግዥ መደቦች ዝርዝር

  • መደብ 1፦ የውሃ መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች (HDPE መገጣጠሚያዎች/Fittings)።

  • መደብ 2፦ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ (1ኛ-8ኛ) ክፍል የሚያገለግሉ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጁ የማጣቀሻ መጽሐፍት።

  • መደብ 3፦ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች (Desktop Computers)።


2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  • በበጀት ዓመቱ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ።

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ እና የቲን (TIN) ቁጥር ሰርተፍኬት።

  • በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ

  • የሰነድ ዋጋ፦ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)

  • የሽያጭ ጊዜ፦ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት

  • የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)፦ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO)።

  • አቀራረብ፦ የጨረታ ሰነዱን ዋና (Original) እና ቅጂ (Copy) በፖስታ አሽጎ ማቅረብ።


4. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ጊዜ

  • መዝጊያ ቀን፦11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት

  • መክፈቻ ቀን፦11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት (በድርጅቱ ዋና ጽሕፈት ቤት)።

  • ማሳሰቢያ፦ 11ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

5. አድራሻና የመገናኛ ስልኮች

  • ቦታ፦ ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፣ ጣይቱ ክፍለ ከተማ፣ ቀይት ቀበሌ።

  • ስልክ ቁጥር፦ 011-656-0249 ወይም 0961 14 07 05

  • ኢሜይል፦ procurement@tesfab.org

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.