የጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች (TLS) ግንባታ ግልጽ ጨረታ
ኢማጂን ዋን ዴይ (Imagine 1 Day – I1D)
የጨረታ መለያ ቁጥር፦ Tig/i1d/Finland/UNICEF/002/2026
ኢማጂን ዋን ዴይ (I1D) በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች (Temporary Learning Spaces – TLS) ግንባታ ብቃት ያላቸውን ተቋራጮች በሦስት ምድቦች (Lots) አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. የግንባታ ቦታዎች ዝርዝር (Lots)
| ምድብ (Lot) |
ወረዳ |
የትምህርት ቤቶች ስም |
| Lot 1 |
ራያ ጨርጨር |
ቀርሶሌ፣ ጻዕዳ ማይዳ፣ ዶዶታ፣ ቁሌታ እና ማሩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች። |
| Lot 2 |
ኮረም |
ቆላ ጽሕዲ እና መስቆተ ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች። |
| Lot 3 |
ዛታ |
ዳራ ማርያም፣ በቀዳ፣ ዲንቃ እና ዳራ ወላኩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች። |
2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
ደረጃ (Grade)፦ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሕንፃ ወይም ጠቅላላ ተቋራጭ (BC/GC Grade 5 & Above)።
-
ልምድ፦ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ 5 ተመሳሳይ የክፍል ግንባታ ፕሮጀክቶችን መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) በኩል ያከናወነ።
-
ሕጋዊ ሰነዶች፦ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የቲን (TIN) ሰርተፍኬት፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የቫት (VAT) ዲክላሬሽን።
-
የሥራ ጊዜ፦ ውል በተፈረመ በ 7 ቀናት ውስጥ ሥራ መጀመርና በ 45 የካላንደር ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ ይኖርበታል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)
4. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና መዝጊያ ቀን
-
የሰነድ ዋጋ፦ የማይመለስ ብር 600.00።
-
ሰነድ መገኛ፦ በመቀሌ በሚገኘው የኢማጂን ዋን ዴይ የትግራይ ክልል ማስተባበሪያ ቢሮ ከመጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (March 30, 2026) ጀምሮ።
-
የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (April 08, 2026) ከጠዋቱ 3:00 (9:00 AM) ሰዓት።
-
የመክፈቻ ጊዜ፦ በዕለቱ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 (9:30 AM) ሰዓት።
5. አድራሻ እና መገናኛ