Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የሽያጭ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 16

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የሽያጭ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 16

Description

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) – ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የሽያጭ ጨረታ

የማስታወቂያ ቁጥር፡ FA-08/2025/26

ባንኩ ለረጅም ጊዜ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን እና ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች

  • አውቶሞቢሎች፦ ቶዮታ ያሪስ (Toyota Yaris)፣ ጂሊ ሳባ (Geely Saba) እና ሊፋን (Lifan)።

  • ሞተር ሳይክሎች፦ ሱዙኪ (Suzuki)።


2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና የምልከታ ፕሮግራም

  • የሰነድ ዋጋ፦ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 ገቢ በማድረግ።

  • የምልከታ ቦታ፦ ሱሉልታ በሚወስደው መንገድ፣ መነአቢቹ ክፍለ ከተማ፣ ሚዛንን አለፍ ብሎ በቻይና ጋራጅ በኩል በሚያስገባው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው አነን ሰላሌ የባንኩ ግምጃ ቤት።

  • የምልከታ ቀናት፦ መጋቢት 04፣ 08፣ 09 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ከጠዋቱ 3፡30 – 10፡00 ሰዓት)።

  • የመዝጊያ ዕለት ምልከታ፦ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም (ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡30 ሰዓት)።


3. ዋና ዋና የጨረታ ደንቦች

  • የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)፦ ተጫራቾች የመነሻ ዋጋውን 10% (አሥር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ስም ማቅረብ አለባቸው።

  • የታክስ ሁኔታ፦ ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸው 15% VAT የሚያካትት ወይም የማያካትት መሆኑን በግልጽ መጥቀስ አለባቸው። ካልተጠቀሰ VAT አካቶ እንደቀረበ ይቆጠራል።

  • አሸናፊነትና ክፍያ፦ አሸናፊው ደብዳቤ ከደረሰው ዕለት ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ክፍያውን መፈጸም አለበት። ካልሆነ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

  • ተጨማሪ ወጪዎች፦ የቦሎ እና የስም ዝውውር ክፍያዎችን አሸናፊው ይሸፍናል።


4. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ጊዜ

  • የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

  • የመክፈቻ ቀን፦ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት (ተጫራቾች በተገኙበት)።

  • ቦታ፦ ቦሌ መንገድ፣ ራንግ ሪል ስቴት ሕንፃ፣ 7ኛ ፎቅ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ።

5. አድራሻና የመገናኛ ስልኮች

  • አድራሻ፦ ራንግ ሪል እስቴት ሕንፃ፣ 7ኛ ፎቅ፣ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ።

  • ስልክ ቁጥር፦ 011 557 61 74

  • ፖ.ሳ.ቁ፦ 16936፣ አዲስ አበባ።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.