You have no bookmark.
ንብረት ቁጥር 1: በባህር ዳር ዲስትሪክት ቅጥር ጊቢ ውስጥ።
ንብረት ቁጥር 2 እና 3: በመቀሌ ዲስትሪክት ቅጥር ጊቢ ውስጥ።
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
ማንኛውም ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25%) በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
የንግድ ማህበር ተወካይ: የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ የያዘና ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል።
ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT): ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ በቀረቡ ንብረቶች ላይ አሸንፎ የገዛ ተጫራች በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
ሌሎች ክፍያዎች: የጨረታ አሸናፊ ከንብረቱ ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
ንብረት መጎብኘት: ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
ቀሪ ክፍያና የንብረት መረከቢያ:
አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ቀሪውን የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
አሸናፊው ክፍያውን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ አለበት። ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፤ ለሚኖር ወጪም ገዢው ኃላፊነት ይወስዳል።
የባንኩ መብት: ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር: 0111-13-05-08
አካል ቀርቦ ማነጋገር: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል።
No products in the cart.
Account details will be confirmed via email.
For faster login or register use your social account.