Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ሐራጅ የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች

Now Open
  • Viewed - 85

ሐራጅ የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች

Now Open
  • Viewed - 85

Description

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

1. በሐራጅ የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር

 

ተራ ቁ. ተበዳሪ/አስያዥ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ ሰሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪ አይነት የስሪት ዘመን (እ.አ.አ) የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ተ.ዕ.ታ.ን ሳይጨምር) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1 ሬድሮክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ ቦሌ መድሃኒአለም አአ-03-B16263 ጃፓን- ሊንከሊን-አውቶሞቢል 2020 15,650,000.00 ብር ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
2 ሬድሮክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ ቦሌ መድሃኒአለም አአ-03-B15111 እንግሊዝ-ሬንጅሮቨር- የመስክ ተሽከርካሪ 2020 15,350,000.00 ብር ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
ማስታወሻ ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደአገር ውስጥ የገቡ ናቸው።

 

2. የሐራጅ አፈፃፀም ቦታና ደንቦች

 

 

ሀ. የሐራጅ ቦታ እና ጊዜ

 

መግለጫ ዝርዝር
የሐራጅ ቀን ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐራጅ ቦታ የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ።
የተፈቀደላቸው ተሳታፊዎች ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ።
የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይከናወናል።

 

ለ. የጨረታ ማስያዣ (Bid Security)

 

  • የማስያዣ መጠን: የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (25%)
  • የማስያዣ ዓይነት: በሕብረት ባንክ አ.ማ. ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ
  • ተቀባይነት የሌለው: ከሲ.ፒ.ኦ. ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ማስያዣ።

 

ሐ. ሌሎች ቁልፍ ደንቦች

 

  • ንብረት መጎብኘት: ተጫራቾች ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች መታወቂያ: ግለሰቦች መታወቂያ፣ የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ደግሞ ዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ ስልጣን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት የተፀደቀ ሰነድ (መመስረቻ ፅሁፍ/ቃለ ጉባኤ/ውክልና) መያዝ ይገባቸዋል።
  • ቀሪ ክፍያ: አሸናፊው ቀሪውን ገንዘብ ባንኩ ከተቀበለው በኋላ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት።
  • ክፍያ አለመፈፀም ቅጣት: በ15 ቀናት ውስጥ ካልተከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤ ሐራጁ ይሰረዛል፤ ንብረቱ በድጋሚ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነትም ይጠየቃል።
  • ተጨማሪ ክፍያዎች: የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።
  • የባንኩ መብት: ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

3. ለተጨማሪ መረጃ መደወያ ቁጥሮች

 

መምሪያ ስልክ ቁጥር
የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ 0115 57 37 72
0114 70 41 03
0114 70 03 15

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.