Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ደረጃ (IFRS)

Now Open
  • Viewed - 112

በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ደረጃ (IFRS)

Now Open
  • Viewed - 112

Description

🧾 ኦሳካ ብረታ ብረት ኃ/የተ/የግ/ማህበር: የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅቱ በአዋጅ ቁጥር 847/2014 እና በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 332/2014 መሠረት የሂሳብ ሥራውን በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ደረጃ (IFRS) ለመመዝገብ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ አካውንቲነግና ኦዲት ቦርድ (AABE) ባስቀመጠው መርሃግብር መሠረት ሥራውን ለመሥራት ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን በጨረታ ይጋብዛል።

📌 የሥራው ዝርዝር

  • ተፈላጊ ሥራ: የድርጅቱን የሂሳብ ሥራ በኢትዮጵያ አካውንቲነግና ኦዲት ቦርድ መርሃግብር መሠረት ወደ IFRS ደረጃ ማሸጋገር (Conversion) እና መመዝገብ።

  • የጨረታ ሂደት: የድርጅቱን ስፋትና የሂሳብ ደረጃ ከግምት ውስጥ ያስገባ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ማቅረብ ያስፈልጋል።

    1. በመጀመሪያ የቴክኒካል ሃሳቡ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ይመረጣል።

    2. በመቀጠልም የፋይናንስ ፕሮፖዛሉ ተከፍቶ አሸናፊው ይወሰናል።

  • ተፈላጊ የሥራ ፍጥነት: ሥራውን ባፋጣኝ ሠርቶ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይፈለጋሉ።

📜 በቴክኒካል ፕሮፖዛል መካተት ያለባቸው ዝርዝሮች

ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡

  1. የህጋዊነት ማረጋገጫዎች (Renewed Licenses):

    • ወቅታዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት።

    • የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት።

    • የታደሰ የሞያ ምዝገባ ሰርተፊኬት (ከAABE ወይም ከሚመለከተው አካል)።

  2. የድርጅት መረጃና ልምድ:

    • የድርጅት አጭር መግለጫና የሥራ ልምድ።

    • የባለሙያዎችን ትምህርትና የሥራ ልምድ የሚያሳይ ሰነድ (CVs)።

  3. የመልካም አፈፃፀም ማረጋገጫ:

    • ቀደም ሲል ከሠሩባቸው ተቋማት ቢያንስ ከሦስት (3) ቦታ የመልካም አፈፃፀም ምስክር ወረቀት።

  4. የአፈፃፀም ስልት:

    • ጥናቱ የሚያጠናበት፣ ስልትና መርሃግብር።

📅 የሰነድ ማስረከቢያ ጊዜና አድራሻ

  • የመጨረሻ ቀን: ይህ ማስታወቂያ በመጨረሻ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰነዶቻችሁን እንድታቀርቡ ይፈለጋል።

  • አድራሻ: ብስራተ ገብርኤል ባይኔ ህንፃ 4ኛ ፎቅ

  • ስልክ ቁጥር: 0113203731 ፣ 0912341645

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.