ባለ 13 ፎቅ (2B+G+13+T) የአፓርታማ ሕንፃ ግንባታ ግልጽ ጨረታ
ታዛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሥራ ማኅበር (Taza Housing Cooperative Association)
ታዛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07 (ሳይት 6.4) ላይ ለሚያስገነባው ባለ ሁለት ቤዝመንት፣ ምድር ቤት እና 13 ፎቅ (2B+G+13+T) የመኖሪያ አፓርታማ ሕንፃ ብቃት ያላቸውን ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
ደረጃ (Grade)፦ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ተቋራጭ (GC-2) ወይም ደረጃ 1 የሕንፃ ተቋራጭ (BC-1) የሆኑ።
-
ሕጋዊ ሰነዶች፦ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የቫት (VAT) ምዝገባ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና በመንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን (FPPPA) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
-
ልዩ ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ለሁለቱም አማራጮች (Lot 1: የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ሥራ እና Lot 2: የሰው ኃይል ብቻ ሥራ) ፕሮፖዛል ማቅረብ አለባቸው። አንዱን ብቻ ማቅረብ ከጨረታው ውጭ ያደርጋል።
2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security)
-
መጠን፦ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)።
-
ዓይነት፦ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee)።
-
ጸናታ፦ ዋስትናው ለ 180 ቀናት የጸና መሆን አለበት።
3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና መዝጊያ ቀን
-
የሰነድ ዋጋ፦ የማይመለስ ብር 2,000.00።
-
የአከፋፈል ሁኔታ፦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000556507547 (ታዛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የ/ሥ/ማ) ገቢ በማድረግ የባንክ ማስታወቂያውን (Advice) በኢሜይል (tazahousinglimitedcoop@gmail.com) በመላክ።
-
የመዝጊያ ቀን፦ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (April 16, 2026) ከቀኑ 8:00 (2:00 Local Time) ሰዓት።
-
የመክፈቻ ጊዜ፦ በዕለቱ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 (2:30 Local Time) ሰዓት።
4. አድራሻ እና መገናኛ
-
ጊዜያዊ ቢሮ፦ ቦሌ ወሎ ሰፈር፣ ተባበር ሕንፃ (Tebaber Building) 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 106B።
-
ስልክ ቁጥር 1 (አቶ አቤል)፦ 0911-41-29-67
-
ስልክ ቁጥር 2 (አቶ ፍጹም)፦ 0911-44-34-58
-
ኢሜይል፦ tazahousinglimitedcoop@gmail.com