የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
የጨረታ ቁጥር: 32/2018
የስራው አይነት: የህንፃ ቤዝመንት የቆሻሻ ፍሳሽ ማጽዳት አገልግሎት
1. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
-
ህጋዊ ሰነዶች: በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የቲን (TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
-
የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond): በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ ነው።
-
የመወዳደሪያ ዋጋ: ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የቫት (VAT) ታክስን ያካተተ መሆን አለበት።
2. የጨረታ ሰነድ አገዛዝ እና የቆይታ ጊዜ
-
የሰነድ ዋጋ: የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)።
-
የመሸጫ ቦታ: ጉርድ ሾላ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ህንፃ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 6።
-
የጨረታው ቆይታ: ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
3. የጨረታ አቀራረብ እና መክፈቻ
-
አቀራረብ: የጨረታ ሰነዱን ዋና (Original) እና ኮፒ (Copy) በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
-
የመዝጊያ ሰዓት: በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።
-
የመክፈቻ ሰዓት: በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
አድራሻ እና ስልክ ቁጥር
ማሳሰቢያ: መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።