You have no bookmark.
የህጋዊነት ሰነዶች: ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡-
በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ።
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት።
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት።
የግብር ክሊራንስ።
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)।
በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ።
በሙያ ዘርፍ የተሰጠ የታደሰ የስራ ፈቃድ።
የሰነድ አቀራረብ: የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እስከ ጨረታ መዝጊያ ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ።
የዋጋ አቀራረብ ዝርዝር: ተጫራቾች ዋጋቸውን ሲያቀርቡ የሚከተሉትን በግልጽ መጥቀስ አለባቸው፡-
በጉዳይ በፐርሰንት: አክሲዮን ማህበሩ በሚያቀርባቸውም ሆነ በሚቀርብበት ክስ ጉዳይ በ1 ጉዳይ በፐርሰንት ምን ያህል እንደሚያስከፍሉ።
ወርሀዊ ቋሚ ክፍያ: በወር የሚጠይቁት ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ምን ያህል እንደሆነ።
የቴክኒክ ማስረጃ: ጫረታውን ቢያሸንፍ ለአክሲዮን ማህበሩ የሚሰጡትን አገልግሎቶች በዝርዝር መጥቀስ አለበት።
ማህተምና ፊርማ: በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር አለበት።
ተገቢ ያልሆነ ጨረታ: አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ።
የአሸናፊ ግዴታዎች:
አገልግሎት በተፈለገ ጊዜ ሁሉ በራሱ ትራንስፖርት ዋና መ/ቤት ወይም አገልግሎቱ በሚካሄድባቸው ሌሎች ቦታዎች ሁሉ በመንቀሳቀስ አገልግሎቱን የመስጠት ኃላፊነት አለበት።
ለሰጠው አገልግሎት ለሚከፈለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ የመስጠት ኃላፊነት አለበት።
የመክፈቻ ቦታ: በአክሲዮን ማህበሩ ዋ/መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 301 ውስጥ (ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት)።
አድራሻ: አዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ጨው በረንዳ ሀዋ ህንፃ 3ኛ ፎቅ የፋ/ግዢ/ንብ/አስ/መምሪያ።
ስልክ ቁጥር: 0922-100056 / 0989-505051
ኢሜይል: anabist2014@gmail.com
anabist2014@gmail.com
ማስታወሻ: በጨረታው መክፈቻ እለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም። አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
No products in the cart.
Account details will be confirmed via email.
For faster login or register use your social account.