Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የሐራጅ ማስታወቂያ

Now Open
  • Viewed - 84

የሐራጅ ማስታወቂያ

Now Open
  • Viewed - 84

Description

ገዳ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/1992 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር

 

 

ሀ. ቋሚ ንብረት (ንግድ ቤት)

 

ተበዳሪ ስም ንብረት አስያዥ ንብረት ዓይነት አበዳሪ ቅርንጫፍ ከተማ ቀበሌ/ወረዳ ቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ቀን (2018 ዓ.ም) ሰዓት
አቶ አድማሱ በቀለ መኩሪያ አቶ አድማሱ በቀለ መኩሪያ የንግድ ቤት አባ መላሻ ሻሻማኔ ቢሻን ጉራቻ 10,000 11,853,304.13 09/03 4:00 – 6:00

 

ለ. ተንቀሳቃሽ ንብረት (መኪና)

 

ተበዳሪ ስም መኪና አይነት የሚገኝበት ቦታ ሰሌዳ ቁጥር የተሰራበት ዘመን የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ቀን (2018 ዓ.ም) ሰዓት
አቶ ቶማስ ጥላሁን ሰቦቃ ቻይና ቢዋይዲ የቤት አውቶሞቢል አዲስ አበባ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ ፊት ለፊት የሚገኝ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 02-አአ-C58982 2024 3,900,000.00 24/02 4:00 – 6:00
ሻንሲ ቁጥር LC0C76C46R4187847 ሞተር ቁጥር BYD472QA824071003

 

2. የሐራጅ ደንቦች እና መስፈርቶች

 

 

ሀ. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security)

 

  • መጠን: የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25%
  • ዓይነት: በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ / ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተመላሽ: ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል

 

ለ. የሐራጅ መካሄጃ እና ምዝገባ

 

  • ቦታ: በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ አከባቢ በሚገኝ ገዳ ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ።
  • ተሰብሳቢዎች: ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። (ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል)።
  • ምዝገባ: የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ በፊት ይጠናቀቃል
  • የጨረታ ሂደት: የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።

 

ሐ. የሕጋዊ አካላት ተሳትፎ

 

  • ድርጅቶች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተረጋግጦ የተመዘገበ የመመስረቻ ፅሁፍ እና እንደአስፈላጊነቱ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለ-ጉባኤዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

መ. የክፍያ እና የአሸናፊ ግዴታዎች

 

  • ማሸነፍ: ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
  • ክፍያ ጊዜ: ያሸነፈ ተጫራች ማሸነፉ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
  • ቅጣት: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል
  • ንብረት ማዘዋወር:
    • አሸናፊው ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀውን ክፍያ ይከፍላል።
    • አሸናፊው ንብረቱ በሚገኝበት ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር በመቅረብ የሊዝ ውዝፍ ክፍያ ካለ ውል መዋዋል አለበት
    • ባንኩ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል

 

ሠ. ንብረት መጎብኘት

 

  • ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘው ለመጎብኘት ይቻላሉ።

 

3. የመገናኛ አድራሻ

 

መግለጫ ዝርዝር
ስልክ ቁጥር (ተጨማሪ መረጃ) 0920885734
የባንኩ መብት ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.