የሦስት ዓመት የሕፃናት አልሚ ምግቦች (RUTF እና RUSF) አቅርቦት ጨረታ
ጎል ኢትዮጵያ (GOAL Ethiopia) የጨረታ መለያ ቁጥር፦ ITT-ADD-ZZ1-48548
ጎል ኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ሰብአዊ እርዳታዎች የሚውል የሕፃናት አልሚ ምግቦችን (RUTF እና RUSF) ለማቅረብ ለሦስት ዓመታት የሚቆይ የውል ስምምነት (Framework Agreement) ለመፈጸም ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ይጋብዛል።
1. የአቅርቦት ዝርዝር (Target Products)
ተጫራቾች የሚከተሉትን አልሚ ምግቦች ለማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፦
2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
ሕጋዊ ሰነዶች፦ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸው አቅራቢዎች።
-
የታማኝነት መርህ፦ ጎል ኢትዮጵያ ከማንኛውም የሙስና እና የማጭበርበር ተግባር የጸዳ አሠራርን ይከተላል። በሂደቱ ላይ ማንኛውም ጥርጣሬ ካለ በ www.safecall.co.uk/report ሪፖርት ማድረግ ይቻላል።
3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና መረጃ
-
የሰነድ መገኛ፦ ተጫራቾች ሙሉ የጨረታ ሰነዱን (Tender Dossier) ከድርጅቱ ድረ-ገጽ goalglobal.org/tenders ላይ ማግኘት ይችላሉ።
-
የማብራሪያ ጥያቄ መዝጊያ፦ ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (April 10, 2026) ከቀኑ 10:30 (4:30 PM EAT) ሰዓት።
-
ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፦ በኢሜይል አድራሻ clarifications@goal.ie በጽሑፍ መጠየቅ ይቻላል።
4. የጨረታ መዝጊያ እና አቀራረብ
-
የመዝጊያ ቀን፦ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (April 14, 2026) ከቀኑ 10:30 (4:30 PM EAT) ሰዓት።
-
ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ኮተቤ ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ፣ ሳንሻይን ሪል እስቴት አጠገብ በሚገኘው የጎል ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት።