Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የተለያዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ (ፕላስቲክ ነክ የሆኑና ያልሆኑ ፤ራዲያተር ፤ኤሲ ኩለር፤ባትሪ፣ ቼርኬ ፣ጎማ ፣የተለያዩ ጋቢናዎች ወዘተ…) ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 395

የተለያዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ (ፕላስቲክ ነክ የሆኑና ያልሆኑ ፤ራዲያተር ፤ኤሲ ኩለር፤ባትሪ፣ ቼርኬ ፣ጎማ ፣የተለያዩ ጋቢናዎች ወዘተ…) ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 395

Description

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ከደንበኞች የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ (ፕላስቲክ ነክ የሆኑና ያልሆኑ ፤ራዲያተር ፤ኤሲ ኩለር፤ባትሪ፣ ቼርኬ ፣ጎማ ፣የተለያዩ ጋቢናዎች ወዘተ…) ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. የጨረታው የጊዜ ሰሌዳ እና መካሄጃ ቦታ

 

ተግባር ቀን ሰዓት ቦታ
የጨረታ ሰነድ መግዣ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ዘወትር በስራ ሰዓት ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋናው መስሪያ ቤት
የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን ህዳር 4 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ዋናው መ/ቤት (ጋራድ ሲቲ ሴንተር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7)
የጨረታ መክፈቻ ቀን ህዳር 4 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ዋናው መ/ቤት (ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት)

 

ንብረት መመልከቻ አድራሻ

 

  • ቃሊቲ 4ዐ/60 ኮንደሚኒየም በኩል ገባ ብሎ በተለምዶ የቆላ ዝንብ አካባቢ (ጨሬ ሰፈር) በሚገኘው ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የተጎዱ ንብረቶች ማከማቻ ቦታ። (የጨረታ ሰነድ መግዣ ደረሰኝ በመያዝ መመልከት ይቻላል)።

 

2. የጨረታው ደንቦች እና መስፈርቶች

 

  1. የጨረታ ሰነድ: የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል።
  2. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
    • ለመጫረት የሚፈልገውን የንብረት ዓይነት እና ያቀረበውን የጨረታ ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ፣ የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 15 በመቶ (15%) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ.ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስም በማስያዝ መወዳደር ይቻላል።
    • ጨረታው በሰም በታሸገ ፓስታ ገቢ መደረግ አለበት።
  3. የክፍያ እና የንብረት አወሳሰድ:
    • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ክፍያ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ አክለው በመክፈል እቃዎቹን መረከብ አለባቸው።
    • በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካልወሰዱ ኩባንያው ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ ገቢ አድርጎ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT):
    • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ ካልገለጹ በቀረበው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል
  5. የግብር ኃላፊነት:
    • ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ወይም ሌላ ክፍያ የሻጩ (የኩባንያው) ኃላፊነት ይሆናል
    • አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ
  6. የተሸናፊዎች ሲ.ፒ.ኦ.: ለጨረታ የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ተመላሽ ይደረግላቸዋል
  7. የኩባንያው መብት: ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ

 

  • ዋና መ/ቤት አድራሻ: ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 ቦሌ ወሎ ሰፈር ጋራድ ሲቲ ሴንተር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7
  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር: 0114-67-44-23 / 46ወይም 0114-70-40-54}

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.