Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ማቅረብ

Now Open
  • Viewed - 19

የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ማቅረብ

Now Open
  • Viewed - 19

Description

የካቶሊክ ረሊፍ ሰርቪስ (CRS) – የኢትዮጵያ ሲድ አክቲቪቲ (ESA)

የኢኖቬሽን እና ቢዝነስ ማፋጠኛ ፈንድ (IBAF) የድጋፍ ጥሪ

የማጣቀሻ ቁጥር፡ CRS-ESA-2026-002

CRS/ESA በግል ባለሀብቶች እና በገበሬዎች የኅብረት ሥራ ዩኒየኖች የሚከናወነውን የድንች ምርጥ ዘር ማባዛትና ማከፋፈል ሥራ ለማጠናከር የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ማቅረብ ይፈልጋል። ይህ ድጋፍ በተለይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ ክልሎች ለሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች የታለመ ነው።

1. የአመልካቾች መመዘኛ (Eligibility)

አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦

  • ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ (CoC)፣ የቲን (TIN) ወይም የቫት (VAT) ሰርተፍኬት ያለው ትርፍ አምጪ ድርጅት ወይም የገበሬዎች የኅብረት ሥራ ዩኒየን።

  • በድንች ምርጥ ዘር ብዜትና ሽያጭ ላይ የሥራ ልምድ ያለው (በወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ የሚረጋገጥ)።

  • ለዘር ብዜት የሚሆን በቂ መሬት (የግል፣ በኪራይ ወይም ከአውት ግሮወር ጋር በውል የተያዘ) ያለው።

  • ቢያንስ 1፡1 (Matching Fund) የገንዘብ ወይም የዓይነት አስተዋጽኦ የማድረግ አቅም ያለው።


2. የፅንሰ-ሐሳብ ማመልከቻ (Concept Note) ይዘት

አመልካቾች ቢበዛ በ3 ገጾች የተቀነባበረ የማመልከቻ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው። ሰነዱ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፦

  • የድርጅቱ መገለጫ፦ ስም፣ አድራሻ (ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ) እና የሥራ ልምድ።

  • የምርት ዕቅድ፦ ባለፈው ዓመት የተሸፈነ የመሬት ስፋት፣ በዚህ ድጋፍ የሚጨመር ተጨማሪ ሄክታር፣ የሚመረቱ የድንች ዝርያዎች እና የሚጠበቅ ምርት (በኩንታል)።

  • የገበያ ስትራቴጂ፦ ደንበኞች እነማን ናቸው? ምርቱ የትና እንዴት ይሸጣል?

  • ማህበራዊና አካባቢያዊ ተፅዕኖ፦ ሴቶችንና ወጣቶችን እንዴት ተጠቃሚ ያደርጋል? አካባቢን ለመጠበቅ ምን ዕቅድ አለ?


3. ማያያዝ የሚገባቸው ሰነዶች

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት።

  2. የብቃት ማረጋገጫ (CoC) እና የቲን/ቫት ሰርተፍኬት።

  3. የመሬት ባለቤትነት ወይም የኪራይ ውል ማስረጃ።

  4. የወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ።


4. አቀራረብ እና የጊዜ ገደብ

አመልካቾች ሰነዶቻቸውን በሚከተሉት መንገዶች ማቅረብ ይችላሉ፦

  • በኢሜይል፦ የተፈረመና የታተመ ሰነድ በፒዲኤፍ (PDF) አድርጎ ወደ ibaf@crs.org በመላክ (Subject line: IBAF Grant Application)።

  • በአካል፦ አዲስ አበባ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 09፣ ስዋዚላንድ መንገድ (እንቁላል ፋብሪካ አደባባይ አጠገብ) በሚገኘው የCRS ቢሮ።

  • የመጨረሻ ቀን፦ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም (March 17, 2026)


ለተጨማሪ መረጃ

  • ስልክ፦ +251 112 788800

  • ኢሜይል፦

ማሳሰቢያ፦ CRS ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.