Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

የጠቅላላ ጥገና አገልግሎት ማዕቀፍ ስምምነት (Framework Agreement) ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 13

የጠቅላላ ጥገና አገልግሎት ማዕቀፍ ስምምነት (Framework Agreement) ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 13

Description

 


የጠቅላላ ጥገና አገልግሎት ማዕቀፍ ስምምነት (Framework Agreement) ጨረታ

የጨረታ መለያ ቁጥር፦ UM2026/06749/ADDI

በአዲስ አበባ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ፣ ለዲፕሎማቲክ ሰራተኞች መኖሪያ ቤቶች (ከ6-12 ቪላዎች)፣ ለኤምባሲው ጽሕፈት ቤት እና ለአምባሳደሩ መኖሪያ ቤት የጠቅላላ ጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ብቁ ኮንትራክተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

1. የአገልግሎቱ ዝርዝር (Scope of Services)

አሸናፊው ኮንትራክተር የሚከተሉትን የጥገና አገልግሎቶች እንዲያቀርብ ይጠበቃል፦

  • የኤሌክትሪክ ሥራዎች፦ የኤሌክትሪክ መስመር እና መሣሪያዎች ጥገና (Electric and Electrical System)።

  • የውኃ እና የፍሳሽ ሥራዎች፦ የውኃ መስመር እና የፍሳሽ ማስወገጃ ጥገና (Water and Drainage)።

  • የሕንፃ ጥገና ሥራዎች፦ አጠቃላይ የሕንፃ ጥገና (General building maintenance)።

  • የአገልግሎት ዓይነቶች፦ መደበኛ ክትትል (Technical Caretaker)፣ ቅድመ-መከላከል ጥገና (Preventive Maintenance) እና የአደጋ ጊዜ ጥሪ (Emergency call-out)።


2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ

  • ሁኔታ፦ ኤምባሲው የጨረታ ሰነዱን በታተመ (Hard copy) መልክ አያቀርብም

  • የማግኛ መንገድ፦ ከኤምባሲው ድረ-ገጽ Procurement and tender – Sweden Abroad ማግኘት ይቻላል።

  • የቆይታ ጊዜ፦ ሰነዱ ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (March 9, 2026) ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በድረ-ገጹ ላይ ይገኛል።


3. የጨረታ አቀራረብ እና የጊዜ ሰሌዳ

  • የመዝጊያ ቀን፦ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም (April 6, 2026) ከቀኑ 10:00 (16:00 hrs) ሰዓት።

  • አቀራረብ፦ በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መመሪያ መሠረት በአካል ማቅረብ ያስፈልጋል።

  • የማስረከቢያ ቦታ፦ ስዊድን ኤምባሲ፣ ያሬድ ጎዳና፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 09፣ የቤት ቁጥር 891።


4. አድራሻ

  • ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ (ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ)።

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.