በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር – የኤሌክትሪክ አመንጪ (ጀነሬተር) ግዥ ጨረታ
በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሥራ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሪክ አመንጪ (ጀነሬተር) በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ዝርዝር (Specification) መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
-
በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
-
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
-
ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆኑ የሥራ ግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ
-
የሰነድ ዋጋ፦ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)።
-
የሽያጭ ጊዜ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት።
-
ቦታ፦ ሳሪስ ካዲስኮ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአካል በመቅረብ።
-
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)፦ ተጫራቾች ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው።
-
አቀራረብ፦ የጨረታ ሰነዱንና ዋጋውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ።
3. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ጊዜ
-
የመዝጊያ ቀን፦ ማስታወቂያው በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ።
-
የመክፈቻ ቀን፦ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
-
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ዕቃውን የሚያስረክቡበትን ጊዜ (Delivery Time) በግልጽ መጥቀስ አለባቸው።
4. አድራሻና የመገናኛ ስልኮች
ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።