You have no bookmark.
ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት: 17/04/2018 ዓ.ም (ታኅሣሥ 17 ቀን 2018 ዓ.ም) ጠዋት 3፡00-4፡00
የሐራጅ ቦታ: በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO):
ማንኛውም ተጫራች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛ (አንድ አራተኛ) በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT):
ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን (ማለትም የካልሲ ማምረቻ ማሽን) በጨረታ አሸንፎ የገዛ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
የወጪ ክፍያ:
የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
የክፍያ እና የይዞታ ጊዜ:
አሸናፊው የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪውን የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
አሸናፊው የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ካጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ አለበት። ካልተረከበ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
ንብረት መጎብኘት:
ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
የድርጅት ውክልና: የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ያስፈልጋል።
ስልክ ቁጥር: 0111-13-05-08
አድራሻ: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው ሕግ ክፍል።
No products in the cart.
Account details will be confirmed via email.
For faster login or register use your social account.