Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 401

ግልጽ ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 401

Description

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪው/አስያዥ ስም የንብረቱ አይነት/አገልግሎት አድራሻ የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1 ተክሌ ኃይሉ ተ/ጊዮርጊስ (ተበዳሪው) G+3 የመኖሪያ ቤት አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 11 191.88 22,734,634.49 17/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡00-4፡00
2 ዱካሌ እና ቤተሰቦቹ ቡና መፈልፈያ እና ማጠቢያ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር (ሃሪፋ ጠ/ን/ኃ/የተ/የግ/ማኅበር) ለንግድ ዓላማ የሚውል ሃዋሳ ከተማ፣ ሐይቅ ዳር ቀበሌ 1501.5 53,445,074.50 17/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00-5፡00
3 አውራጃ እና ቤተሰቡ የቡና መፈለፈያ እና ማበጠሪያ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር (አቶ ዱካሌ ዋቀዮ ዳኩሌ) ለንግድ ዓላማ የሚውል G+2 ሕንፃ ሃዋሳ ከተማ፣ ምሥራቅ ቀበሌ 1,665 23,752,467.62 17/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 5፡00-6፡00
4 ተስፋዬ ስብሐቱ ገብረእየሱስ (ተበዳሪው) መኖሪያ ቤት መቀሌ ከተማ፣ ዓዲ ሓቂ ክ/ከተማ 140 4,094,133.45 18/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡00-4፡00
5 ዋጋዬ ካሳዬ ሙላት (ተበዳሪው) መኖሪያ ቤት አርባምንጭ ከተማ፣ ውኃ ምንጭ ቀበሌ 275 3,107,967.50 18/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00-5፡00
6 ዋጋዬ ካሳዬ ሙላት (ወ/ሮ አቦዘነች አሰፋ ወንድምነህ) መኖሪያ ቤት አርባምንጭ ከተማ፣ ውኃ ምንጭ ቀበሌ 297.23 5,580,113.30 18/03/2018 ዓ.ም ጠዋት 5፡00-6፡00

 

2. የሐራጅ መካሄጃ ቦታ እና ሰነድ አወሳሰድ

 

  • የሐራጅ ቦታ: አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ቁጥር 4203
  • የጨረታ ሰነድ: ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰሜን ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንጻ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር 6ኛ ፎቅ እና ንብረቶቹ በሚገኙበት የባንኩ ቅርንጫፎች መውሰድ ይቻላል።

 

3. የጨረታ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (CPO):
    • ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (አንድ አራተኛ) በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው
  2. የንግድ ማኅበር ተጫራቾች: የንግድ ማኅበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ አለበት።
  3. የዋጋ ማቅረቢያ:
    • ተጫራቾች ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ቅጽ ላይ ካሰፈሩ በኋላ፣ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታው አሸናፊ ከባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
    • በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያውን ካልፈፀመ፣ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
    • በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል
  5. ግብር እና ወጪዎች:
    • ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ገዢ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል
    • የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ እና ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል
  6. የንብረት አወሳሰድ:
    • አሸናፊ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ አለበት። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
  7. ንብረት መጎብኘት: ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
  8. የብድር አቅርቦት: ባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል
  9. የባንኩ መብት: ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

4. የእውቂያ መረጃ

 

  • ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር: 0111-13-05-08
  • አካላዊ መገኘት: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.