Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 87

ግልጽ ሐራጅ

Now Open
  • Viewed - 87

Description

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚቀርብ ንብረት ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አድራሻ (ከተማ/ክ/ከተማ) የይዞታው ስፋት (ካ.ሜ) የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)
1 ጉጂ ሃይላንድ ኮፊ ፕላንቴሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ወይ እቴነሽ መለሰ ፈንቴ አዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክ/ከተማ 380 ቅይጥ አገልግሎት (ሕንፃ) 16,053,645.36

 

የጨረታው ቀንና ሰዓት

 

  • ቀን: 16/03/2018 ዓ.ም
  • ሰዓት: ጠዋት 3፡00-4፡00 (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)

 

2. የሐራጅ ደንቦች እና መስፈርቶች

 

 

ሀ. የጨረታ ማስከበሪያ እና ቦታ

 

  • የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond): የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (አንድ አራተኛ)።
  • የማስከበሪያ ዓይነት: በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ። (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።)
  • የጨረታ መካሄጃ ቦታ: በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ቁጥር 4203

 

ለ. የንብረት ጉብኝት

 

  • ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሠረት መጎብኘት ይቻላል።

 

ሐ. የአሸናፊ ግዴታዎች

 

  • ተጨማሪ እሴት ታክስ: አሸናፊው በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
  • ሌሎች ክፍያዎች: አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
  • የክፍያ ጊዜ: ከፍተኛ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊ ስለመሆኑ የሚገልጽ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
  • ቅጣት: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ፣ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል

 

መ. ንብረት መረከብ

 

  • አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ አለበት።
  • በ15 ቀናት ውስጥ ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፤ ከንብረቱ ጥበቃ ጋር ለሚኖር ወጪም ገዢው ኃላፊነቱን ይወስዳል

 

ሠ. የንግድ ማህበራት ተሳትፎ

 

  • የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻና መተዳደርያ ደንብ የያዘና ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን አለበት።

 

3. የመገናኛ አድራሻ እና ማስታወሻ

 

  • ለተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 011-113-05-08 መደወል ይቻላል።
  • የባንኩ መብት: ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.