Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 449

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 449

Description

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸዉንና በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/መያዣ ሰጪ ስም የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት የቦታው ስፋት (ካ.ሜ) ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታው መነሻ ዋጋ (ብር)
1 ገዳ የእንጨት… (ተበዳሪዉ) የኢንዱስትሪ ሕንፃ 3,118.37 ሸገር ከተማ፣ ሱሉልታ ክ/ከተማ 25,643,124.70
2 ገዳ የእንጨት… / አቶ አበበ ሰቦቃ የመኖሪያ ቤት 400 ሸገር ከተማ፣ ሱሉልታ ክ/ከተማ 9,257,093.90

 

የጨረታው ጊዜ እና ቦታ

 

ተ.ቁ የንብረቱ አይነት የጨረታው ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታ ሰዓት
1 የኢንዱስትሪ ሕንፃ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም 4:30 – 5:30 5:30 – 6:00
2 የመኖሪያ ቤት ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 – 9፡30 9፡30 – 10፡00
  • የጨረታ ቦታ: አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ

 

2. የሐራጅ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (CPO):
    • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይችላሉ።
  2. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ዋጋውን አጠቃሎ መክፈል አለበት።
    • ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
  3. ግብር እና ወጪዎች:
    • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ገዢው ይከፍላል
    • ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን፣ ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል
  4. ብድር: የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል
  5. ንብረት መጎብኘት: ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል
  6. መገኘት: ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል
  7. የባንኩ መብት: ባንኩ የተሻለ አማራጭ/መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ

 

  • ስልክ ቁጥር: እና (አዲስ አበባ)
  • ድርጅት: አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.