Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

Description

ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለ) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪ/አስያዥ ስም የንብረቱ አድራሻ (ከተማ/ክ/ከተማ/ወረዳ) የቦታ ስፋት (ካ.ሜ) የንብረቱ ዓይነት የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጅ ቀን የሐራጅ ደረጃ
1 ወ/ይ አፎሚያ ታደለ ምንይዋብ አ.አ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ቦሌ አራምሳ ሳይት 10፣ ብሎክ 434 37.16 ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ (መኖሪያ ቤት) 2,220,634.51 ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በድጋሚ
2 አቶ ወግደረስ መራ እጅጉ አ.አ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ጀሞ 1 ሳይት 01፣ ብሎክ 28 30.31 ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ (መኖሪያ ቤት) 2,365,575.02 ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በድጋሚ
3 አቶ አቤል ሙሀመድ ይመር አ.አ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ገላን ሳይት 04፣ ብሎክ 159 30.31 ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ (መኖሪያ ቤት) 2,056,606.61 ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በድጋሚ
4 አቶ ግርማ ለገሰ ሚጀና ሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዪ ፈጩ ክ/ከተማ 09፣ ብሎክ 773 37.16 ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ (መኖሪያ ቤት) 1,785,404.93 ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በድጋሚ

 

የጨረታ ሰዓቶች

 

ተ.ቁ የሐራጅ ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታው ሰዓት
1 እና 3 ህዳር 18 እና 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3:30 – 5:00 ጠዋት 5:00 – 5:50
2 እና 4 ህዳር 18 እና 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 7:30 – 9:00 ከሰዓት 9:00 – 9:50

 

2. የሐራጅ ደንቦች እና ግዴታዎች

 

  1. የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ):
    • ተጫራቾች የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ ብቻ መጫረት ይችላሉ።
  2. የመክፈያ ጊዜ:
    • አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
  3. የቅጣት ድንጋጌ:
    • አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ካላከናወነ፣ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል
    • ንብረቱ እንደገና ለጨረታ ሲቀርብ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ፣ የዋጋ ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍል ይጠየቃል
  4. መገኘት:
    • ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።
  5. የተጫራቾች ስነ-ስርዓት:
    • የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም
    • ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም። ይህንን ደንብ የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።
  6. ተጨማሪ ክፍያዎች (ግብር):
    • ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም የልማት ገንዘብ ክፍያ እና ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ በሙሉ (ታክስ፣ ቫት፣ የስም ማዛወሪያ ወዘተ…) በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።
    • ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፣ ነገር ግን የስም ዝውውር ክፍያዎችን ገዥው ይከፍላል
  7. ብድር ማመቻቸት:
    • የባንኩን የብድር ፖሊሲ የሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋ መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል። ነገር ግን ብድር አለመፈቀዱ አሸናፊው ከላይ የተቀመጡትን ግዴታዎች አያስቀርም።
  8. የባንኩ መብት:
    • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. አድራሻ እና የእውቂያ መረጃ

 

  • የሐራጅ መካሄጃ ቦታ: ሰንጋተራ በሚገኝው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ
  • ንብረት መጎብኘት: ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መጎብኘት ይችላሉ።
  • ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥሮች: 011-6-68 62 16 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48
  • አድራሻ: Mexico, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia.

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.